ጥር 05/2018 ዓ.ም
በአሜሪካ ፍሎሪዳ በተካሄደው 46ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው እና አኩሪ ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ ጠዋት አዲስአበባ ገብተዋል።
ቡዱኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚንስትር ሚኒስቴር ክብርት ሸዊት ሻንካ፣ የስፖርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታው ክቡር መኪዩ ሙሀመድ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ፣የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፣የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።
በተጨማሪም አሜሪካ ፍሎሪዳ ድረስ በመገኘት አትሌቶችን ያበረታታው፣የአትሌቲክስ ልምዱና ተሞክሮውን በማካፈል ፣ ድሉ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ያበረከተው የዓለም አገር አቋራጭ ንጉሱ ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከቡድኑ ጋር አብሮ ተመልሰዋል ።
በሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ ፣2 ብር እና 2 የነሃስ ሜዳሊያ በማስመዝገብ ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።






