በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪክ አዲስ ስኬት የሚመዘገብበት ታላላቅ ሥራዎች በቀጣይ ሳምንታት ይከናወናሉ :-ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

መጋቢት 12፣2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪክ አዲስ ስኬት የሚመዘገብበት ኮንቲኔንታል ቱር ጨምሮ በ55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲሁም በ29ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዙሪያ ለሚዲያ አካላት ዛሬ በማግኖሊያ ሆቴል መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪክ አዲስ ስኬት የሚመዘገብበት ታላላቅ ሥራዎች በቀጣይ ሳምንታት እንደሚከናወኑ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቀዋል ።

በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄዳው ኮንቲኔንታል ቱር አንዱ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

በሀገራችን የሚካሄደው ኮንቲኔንታል ቱር ከዓለም አትሌቲክስ ጋር ያለን ግንኙነት እንዲጠናከር፤ የሀገራችንን የስፖርት ዲፕሎማሲ አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ያለንን አቅም ለዓለም ማሳየት የሚያስችል መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አመላክተዋል።

ውድድሩ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ከመሆኑ የተነሳ ወደፊት ደረጃውን ከ“Bronze Level” ወደ “Gold Level” ለማሳደግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።

ኢትዮጵያ በ2029 እና በ2031 የሚካሄደውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማስተናገድ በጨረታ ሂደት ውስጥ በንቃት ተሳትፎ እያደረገች እንደሆነም በመግለጫው ተመላክቷል።

የ2028 የዓለም አትሌቲክስ አልትሜት ሻምፒዮንሺፕ ለማዘጋጀት እየተከናወኑ ያሉ የጨረታ ሂደቶች ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑም ፕሬዚዳንቱ ጠቁሟል።

Categories: Uncategorized