በታላቅ ድምቀት በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ !

#

የካቲት 7/2018 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻ ዕዝ የተመሰረተበትን 65ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል

በውድድሩ ላይ በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ 222 ወንዶች፣ 80 ሴቶች በድምሩ 302 ኤሊት አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳትፈዋል ።

በተጨማሪም ከ10,000 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች በውድድሩ ላይ መሳተፍ ችሏል ።

በውድድሩ ከ1-5 አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ከፍተኛ የተባለውን የገንዘብ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል ።

በዚህም መሰረት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ውጤት :-

የወንዶች ውድድር

1ኛ አትሌት ቢኒያም መላክ ከፀደይ ባንክ 500 ሺህ ብር
‎2ኛ አትሌት ሣሙኤል ፍሬው ከሲዳማ ቡና 250 ሺህ ብር
3ኛ አትሌት አብዱሰላም ወርቁ በግል 100 ሺህ ብር

በሴቶች ውድድር

1ኛ አትሌት ውድነሽ ዓለሙ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 500 ሺህ ብር
‎2ኛ አትሌት ፅጌ ገብረስላማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 250 ሺህ ብር
3ኛ አትሌት ዝማም ማራኪ በግል 100 ሺህ ብር አሸንፈዋል።

እንደዚህ ዓይነት የውድድር እድሎች በስፋት ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ፣ ተተኪ አትሌቶች እንዲፈሩ የሚያስችሉ መሆናቸውንና ሽልማቱ ፣ አትሌቱን የበለጠ የሚያበረታታ እንደሆነ ተጠቁሟል ።

https://www.facebook.com/share/1AgzTYzbrT/?mibextid=wwXIfr

Categories: Uncategorized