በ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክለው ልዑክ ቡድን ዛሬ ጥዋት ወደ ስፍራው አቅንቷል ።
#########################
ግንቦት 02/2018 ዓ.ም
በበጋና አክራ ከተማ በተዘጋጀው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የሚሳተፈው ልዑክ ቡድን ዛሬ ጠዋት 2:40 ከቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመነሳት ከሰዓታት በረራ በኋላ በውድድሩ ቦታ ይደርሳል።
አርብ ዕለት ሽኝት የተደረገለት ልዑክ ቡድኑ
31 ሴቶች እና 32 ወንዶች አጠቃላይ በድምሩ 63 አትሌቶች እና 12 አሰልጣኞችን በመያዝ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ይጠበቃል።
በተጨማሪም በልዑክ ቡድኑ ውስጥ 3 የህክምና ባለሙያ ፣ 3 የሚዲያ ባለሙያ ፣ 1 የቴክኒክ ቡድን መሪ እና የቡድን መሪ ጨምሮ 6 ኦፊሻል ወደ ስፍራው ያቀናሉ።
ኢትዮጵያ በካሜሮን ዱዋላ በተደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ5 ወርቅ 4 የብር እና 1 የነሃስ አጠቃላይ 10 ሜዳሊያ በመሰብሰብ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ሲደርግ ቆይቷል።
ሻምፒዮናው ከግንቦት 4 እስከ 9 ባሉት ተከታታይ ቀናት የሚደረግ ይሆናል።
🛫 መልካም ጉዞ !
🇪🇹መልካም እድል !



