በ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ።

።።።።።።።።።።።።

ጥር 16/2018 ዓ.ም ሐዋሳ

1ኛውን የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድርን አስመልክቶ በውድድሩቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄዷል ።

በውይይቱም አቶ ዶማርሶ ዶና የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር፣ አቶ ብዙነህ ታቦት የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮምሽነር እና አቶ ንጉሴ ወርቁ የሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ተገኝተዋል።

አቶ ዶማርሶ ዶና የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ስፖርትን ጨምሮ በሁሉም ስፖርቶች መነቃቃት እያሳየ እንደሆነ ገልፀዋል።

አቶ ቡዝነህ ታቦታ የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮምሽነር በበኩላቸው ውድድሩ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሄዱ ለየት እንደሚያደርገው በመግለፅ ለቀጣይ ውድድሮች በር ከፋች ውድድር መሆኑን ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ንጉሴ ወርቁ ለውድድሩ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳሬይክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው ፣ አቶ ብስራት ለጥይበሉ የፌዴሬሽኑ የውድድር ተሳትፎ ከፍተኛ ባለሙያ እና አቶ አሸብር ደምሴ የውድድር ተሳትፎ ባለሙያ ፣ በየተራ ስለ 1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድር በሁሉም መስክ ስለሚሰሩ እና ስለተሰሩት ስራዎች እንዲሁም ስለ ቴክኒካል ጉዳዬች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

በውድድሩ ቴክኒካል ጉዳዮች ዙሪያ ከዳኞች፣ ከክለብ አመራር፣ ከቡድን መሪዎች፣ ከአሰልጠናኞች እንዲሁም ውድድሩን ከሚያግዙ ባለድርሻ አካላት በተነሱ ጥያቄዎች ዙርያ ውይይት ተደርጓል።

1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድር ነገ ጥር 17/2018ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

Categories: Uncategorized