#

የካቲት 8/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዓለም አቀፍ ስፖንሰር ከሆነ የአዲዳስ ካምፓኒ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

የአዲዳስ ካምፓኒ የስፖርት ዳይሬክተር ሚስተር ስፔንሰር ባርደን የተመራ ልዑክ ቡድን በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው የአደይአበባ ዓለምአቀፍ የመለማመጃ ትራክ እና በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስቴዲየም ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም ዳይሬክተሩ እና ልዑኳቸው በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ እና በአዲዳስ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሁለት ፕሮጀከት የአትሌቲክስ ሰልጣኞች ጋር ውይይት አካሂዷል ።

ጉብኝታቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጀመረውን ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተመላክቷል።

Categories: Uncategorized, ዜና