የኢ.አ.ፌ. ጠቅላላ ጉባኤ የፌዴሬሽኑ የበላይ አካል ሆኖ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡፡

 1. የክልል/የከተማ አስተዳደሮች አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወይም የተወከለ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል (በድምጽ)
 2. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በድምጽ ይሳተፋሉ፡፡ ሆኖም የኃላፊነት ጊዜያቸውን አጠናቀው አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ በሚደረግበት ወቅት ድምጽ የመስጠት መብት አይኖራቸውም፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ተወካዮች ውስጥ 2ቱ ብቻ በምርጫ ሂደት ድምፅ በመስጠት ይሳተፋሉ፡፡ (1 ወንድና 1 ሴት)
 3. ከአትሌቶች ማህበር ሁለት ተወካዮች በጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ (አንድ ወንድና አንድ ሴት) (በድምፅ)
 4. ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዳኞች ማህበር አንድ ተወካይ ተሣታፊ ይሆናል፡፡ (በድምፅ)
 5. ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ማህበር አንድ ተወካይ ተሣታፊ ይሆናል፡፡ (በድምፅ)
 6. የየክልል/ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች  አምስትና  ከአምስት በላይ ክለቦች ያደራጁ ከሆነ  የተደራጁት ክለቦች በጥምር ማህበር በማቋቋም ተወካያቸውን በጠቅላላ ጉባዔ ወክለው ይሳተፋሉ፡፡ (በድምፅ)
 7. በክልሉ/በከተማ አስተዳደሩ ስፖርትን የሚመራው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አንድ ኃላፊ (ያለ ድምፅ)
 8. በጠቅላላ ጉባኤ የተሰየመ ኦዲተር (ያለ ድምፅ)
 9. በጠቅላላ ጉባኤ የተሰየሙ የክብር አባላት (ያለ ድምፅ)
 10. የኢፌዲሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርን የሚወክል አንድ ተወካይ (ያለ ድምፅ)
 11. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ኃላፊ ፀሐፊና አባል ሆኖ ይሳተፋል፡፡ (ያለድምፅ)
 12. የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዳይሬክተር በአስረጅነት ይሳተፋል፡፡ (ያለ ድምፅ)
 13. የአበረታች መድሀኒትና ቅመማ ቅመሞች መከላከያና መቆጣጠርያ ጽ/ቤት አንድ ተወካይ (ያለ ድምጽ)
 14. የፌዴሬሽኑ የህግ ባለሙያ (ያለ ድምጽ)
 15. እንደአስፈላጊነቱ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔ ለስፖርቱ ካላቸው ተጨባጭ አስተዋፅዎ አንፃር በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ የሚጋበዙ አካላት/ድርጅቶች ተወካይ ያለድምፅ ሊሳተፉ ይችላሉ፡፡