
ሎሬት ኮሎ/አትሌት ደራርቱ ቱሉ
ፕሬዝዳንት
- ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና
- አንድ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና
- ሁለት ጊዜ የአገር አቋራጭ ሻምፒዮና
- ሁለት ጊዜ የአህጉራት ዋንጫ ሻምፒዮና
- አንድ ጊዜ የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና
- ሁለት ጊዜ የአፍሪካ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና

ዶ/ር በዛብህ ወልዴ
አቃቤ ንዋይ
- የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ በመሆን ለሰባት አመታት አገልግለዋል
- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሃፊ በመሆን ለሰባት አመታት አገልግለዋል
- የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል ሆነው አገልግለዋል
- የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል
- በአትሌቲክሱ ዘርፍ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች አበርክተዋል

አቶ በላይነህ ክንዴ
አባል
- የኢትዮጵያ ሆቴል አትሌቲክስ ክለብ ባለቤት (ሰከላ ወረዳ)
- በተለያዩ ጊዜያት ብሄራዊ የአትሌቲክስና የእግርኳስ ቡድኖችን ስፖንሰር አድርገዋል
- የባህርዳና የወለጋ ስቴዲየም እንዲገነባ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል
- የትምህርና የጤና ተቋማትን በመገንባትና ሲገነቡ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ሌሎች ሃላፊነቶችን በመወጣት ላይ ናቸው

ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ
አባል
- የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ
- በጋዜጠኝነት የ7 ዓመት የስራ ልምድ
- በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በአፋርኛ ቋንቋ የስፖርትና የመዝናኛ ዘርፍ ፕሮግራም አዘጋጅና ቡድን መሪ በመሆን በማገልገል ላይ ያሉ