በተከለከሉ አበረታች መድሃኒቶች አጠቃቀም ዙሪያ የተላለፈ እገዳ፤
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ጽ/ቤት ህዳር 27/2011 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አትሌት አብሰኔ ዳባ ጨመዳ እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 5/2017 በቻይና ፒዦ ከተማ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር በተካፈለችበት ወቅት በቻይና የፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ጽ/ቤት በተደረገላት ምርመራ Higenamine(S3:Beta-2-Agonists) የተባለና በስፖርት የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅማ በመገኘቷ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ጽ/ቤት አትሌቷ ለ4 አመታት ከማንኛውም የአትሌቲክስ ስፖርት መታገዷን ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም አትሌቶቻችን ፌዴሬሽኑ በየጊዜው የሚሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲከታተሉና ከእንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር ራሳቸውን እየጠበቁ ተፈጥሯዊ የማሸነፍ አቅማቸውን በዘመናዊ ስልጠና እያስደገፉ ውጤታማ ከመሆን ውጪ ሌሎች አማራጮችን በፍጹም እንዳይከተሉ እያሳሰበ የጽ/ቤቱን ውሳኔ እንደሚደግፍ ጽኑ አቋሙን ያስታውቃል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ... See more