Loading Events

« All Events

 • This event has passed.

37ኛው የሻ/ል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር

June 3 @ 8:00 am - 5:00 pm UTC+3

37ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሕግና ደንብ

አንቀጽ አንድ

ዓላማ

 

 1. ለክልልና ከተማ አስተዳደር ክለብና የግል የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች የአገር ውስጥ የውድድር ዕድል በመፍጠርና ተተኪ የማራቶን አትሌቶችን ለማፍራት፤
 2. በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ በክለቦች ወዘተ… መካከል የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤
 3. አትሌቶችን ተመጣጣኝ ሽልማት በማዘጋጀት ለማበረታት፤

 

አንቀጽ ሁለት

አጠቃላይ የውድድሩ ደንብ

 

 1. ይህ ውድድር 37ኛው የሻ/ል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ተብሎ ይጠራል፡፡
 2. 37ኛውን የሻ/ል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው፡፡
 3. ውድድሩ የሚመራው በIAAF እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህግና ደንብ ነው፡፡

 

አንቀጽ ሦስት

የውድድሩ ርቀት፣ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

 

 1. የውድድሩ ርቀት 42.195 ኪ.ሜ. ነው፡፡
 2. ውድድሩ የሚካሄደው ሰኔ 6/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል::
 3. ውድድሩ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ ነው::

 

አንቀጽ አራት

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

 

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፡፡ ቁጥሩ የሚለጠፈው በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ ያለመወዳደሪያ ቁጥር መወዳደር አይቻልም፡፡ የመወዳደሪያ ቁጥር በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

 

አንቀጽ አምስት

አለባበስ

 

ማንኛውም አትሌት የክልሉን፣ የከተማ አስተዳደሩን የክለቡን ወይም የተቀሙን መለያ የሆነውን የስፖርት ልብስ መልበስ አለበት፡፡ ማልያ ለብሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፡፡ ተካፍሎ ቢገኝ የግሉም ሆነ የቡድኑ ውጤት ይሰረዛል፡፡

 

 

 

አንቀጽ ስድስት

ተሳታፊዎች

 

ውድድሩ በሁለቱም ፆታ በሴትና በወንድ ተከፍሎ ሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና የግል አትሌቶች ይሳተፋሉ እንዲሁም አንጋፋ አትሌቶች/ቬትራን/ በ21 ኪ.ሜ በግማሽ ማራቶን እንዲሁም የተሳትፎ ተወዳዳሪዎች የ10ኪ/ሜ ይሳተፋሉ፡፡

አንቀጽ ሰባት

ምዝገባ

 1. እያንዳንዱ ተወዳዳሪ ቡድን በሁለቱም ፆታ ከ4-12 አትሌቶች ማስመዝገብ ይችላል፡፡
 2. የምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 25/2013 እስከ ሰኔ 2/2013 ዓ.ም. ድረስ ይሆናል፡፡ ዘግይተው የሚመዘገቡ ክልሎች እና ክለቦች ሰኔ 3/2013 ዓ.ም. ብቻ እስከ 11፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ከቀነ ገደቡ ውጪ ምዝገባ አይከናወንም፡፡
 3. ለውድድሩ ተመዝግበው የማይሳተፉ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማት በቂ ምክንያት ወይም ማብራሪያ ካላቀረቡ በስተቀር ብር 1,000.00 (አንድ ሺ ብር) ይቀጣሉ፡፡

አንቀጽ ስምንት

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ1 ሰዓት በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሁኔታን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፋ በሆነ በ30 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው ለውድድሩ ዋና ዳኛ (refree) በቃል በአትሌቱ፣ በአሠልጣኙ ወይም በቡድን መሪው አማካይነት ሊሆን ይችላል፡፡ የውድድር ዳኛው ውሳኔ መስጠት ወይም ጉዳዩን ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዋና ዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ጋር ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ዳኛው ውሳኔ በሰጠ በ30 ደቂቃ ውስጥ ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡
 5. በክስ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሁፍ ከ1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ ጋር ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፤ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
 6. ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ወይም በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ሆኖ ክሱ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

ያልተገባ ፀባይ

 

ማንኛውም አትሌት፣ አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ወጌሻ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ውድድሩ በሚከናወንበት ወቅት ያልተገባ ፀባይ ካሣየና ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ወይም የውድድር አዘጋጆች ሪፖርት ቀርቦ ጥፋቱ ከተረጋገጠ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተዘጋጀው የአሠልጣኞች፣ አትሌቶችና የክለቦች የሥነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ አስር መሠረት ይቀጣል፡፡

 

 

አንቀጽ አስር

የግል/የቡድን ውጤትንና ሽልማትን በተመለከተ

 

 1. ማንኛውም ተወዳዳሪ ክልል ወይም ክለብ በአንድ ላይ በመወዳደር በሚያስመዘግቡት ውጤት ወይም ደረጃ መሠረት ውጤታቸው ይመዘገባል፡፡ በቡድን ውጤት አሰጣጥ ከአነስተኛ ወደ ከፍተኛ ቁጥር የገባበት ደረጃ ተደምሮ አነስተኛ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡ ሁለት ቡድኖች የውጤት ድምራቸው እኩል ከሆነ መጨረሻ ነጥብ ያስመዘገበ ወይም ለአንደኛው የቀረበ አትሌት ቡድን የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡

 

ለምሳሌ፡- 1.             ቡድን ሀ. 1ኛ፣ 5ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ቢወጡ ድምራቸው 26 ይሆናል፡፡

ቡድን ለ. 2ኛ፣ 3ኛ፣ 6ኛና 1ዐኛ ቢወጡ ድምራቸው 21 ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት የ“ለ” ቡድን የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የውጤት ድምራቸው እኩል ቢሆን መጨረሻ ነጥብ ያስመዘገበ (ዘጊው አትሌት) ማለት ለአንደኛው የቀረበ አትሌት ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡

ለምሳሌ፡-2.  ቡድን ሀ. 1ኛ፣ 5ኛ፣ 8ኛና 9ኛ ቢወጡ ድምራቸው 23 ይሆናል፡፡

ቡድን ለ. 2ኛ፣ 3ኛ፣ 6ኛና 12ኛ ቢወጡ ድምራቸው 23 ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ቡድኖች ነጥባቸው እኩል ቢሆን ለአንደኛው የቀረበው የመጨረሻው (ዘጊው አትሌት) 9ኛ የወጣ የ“ሀ” ቡድን ስለሆነ የ“ሀ” ቡድን የውድደሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡

 1. ለእያንዳንዱ ቡድን ለውድድር ከተመዘገቡት 12 አትሌቶች በቅድሚያ ውድድሩን ላጠናቀቁ “4” አትሌቶች ብቻ የደረጃ ውጤት ይያዛል፡፡
 2. ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ ለሁለቱም ፆታዎች
  • የወርቅ ፤የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል::
 3. በሁለቱም ፆታ ከ1ኛ-10ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 4. ለአሸናፊ ቡድኖች በሁለቱም ፆታ የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል፡፡

የሽልማት መጠን

ደረጃ ለወንዶች   ደረጃ ለሴቶች
1ኛ 50,000 ብር   1ኛ 50,000 ብር
2ኛ 40,000 ብር   2ኛ 40,000 ብር
3ኛ 30,000 ብር   3ኛ 30,000 ብር
4ኛ 25,000 ብር   4ኛ 25,000 ብር
5ኛ 20,000 ብር   5ኛ 20,000 ብር
6ኛ 15,000 ብር   6ኛ 15,000 ብር
7ኛ 12,000 ብር   7ኛ 12,000 ብር
8ኛ 10,000 ብር   8ኛ 10,000 ብር
9ኛ 8,000 ብር   9ኛ 8,000 ብር
10ኛ 6,000 ብር   10ኛ 6,000 ብር
ድምር     216,000.00   ድምር    216,000.00
         
ቬትራን ከ5ዐ ዓመት በታች   ቬትራን ከ5ዐ ዓመት በላይ
1ኛ 7,000 ብር   1ኛ 7,000 ብር
2ኛ 5,000 ብር   2ኛ 5,000 ብር
3ኛ 4,000 ብር   3ኛ 4,000 ብር
4ኛ 3,000 ብር   4ኛ 3,000 ብር
5ኛ 2,000 ብር   5ኛ 2,000 ብር
ድምር     21,000   ድምር     21,000

 

 

አንቀጽ አስራ አንድ

የተወዳዳሪ ለውጥ

 

የተወዳዳሪ ለውጥ የሚደረገው ውድድሩ ከመደረጉ ከአንድ ቀን በፊት እስከ ቀኑ 6፡00 ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሚጠየቀው ቅያሪ ተቀባይነት የለውም፡፡

 

አንቀጽ አስራ ሁለት

ዕድሜ

 

ማንኛውም የማራቶን ተወዳዳሪ ዕድሜው 2ዐ ዓመት እና ከዚያም በላይ መሆን አለበት፡፡ ዕድሜው ከ2ዐ ዓመት በታች የሆነ ተወዳዳሪ በውድድሩ መሳተፍ አይችልም፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

የአትሌቱ ጤንነት

 

በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተሟላ አትሌት ተሰልፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው ክልሉ/ከተማ መስተዳድሩ፣ ክለቡ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡

 

አንቀጽ አራት

የኮቪድ -19 ምርመራ

ማንኛውም በውድድሩ የሚካፈል አትሌት፣ አሠልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ሐኪምና ወጌሻ ወዘተ… ለውድድሩ ከመምጣቱ በፊት በሚኖርበት ክልልና ከ/አስተዳደር ህጉና ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት የኮቪድ -19 ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪም የፊት መሸፈኛ (Face Mask) እና የእጅ ማጽጃ (Sanitizer) መያዝ አለበት፡፡

ማንኛውም በውድድሩ የሚካፈል ክልል ከተማ አስተደደር ክለብና ተቋም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲሁም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለኮቪድ -19 ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ከዉድድሩ ቀን ከ48-72 ሰዓት በፊት መጠናቀቅ አለበት

 

 

አንቀጽ አስራ አምስት

በስም ጥሪና ሽልማት ቦታ በሰዓት መገኘት

 

 1. ማንኛውም ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ45 ደቂቃ በፊት በስም ጥሪ ቦታ በመገኘት ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይኖርበታል፤ በስም ጥሪ ቦታ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡
 2. ተሸላሚ አትሌቶች በሽልማት ቦታ ላይ የክልላቸውን፣ የከተማ አስተዳደራቸውን፣ የክለባቸውንና የተቋማቸውን መለያ ለብሰው መቅረብ አለባቸው፡፡
 3. የሜዳሊያም ሆነ የገንዘብ ተሸላሚዎች በሽልማት ቦታና ሰዓት ካልተገኙ ሽልማቱ አይሰጣቸውም ፡፡ ነገር ግን ያስመዘገቡት ውጤት ለቡድናቸው ይመዘገባል፡፡

 

 

አንቀጽ አስራ ስድስት

የቴክኒክ ስብሰባ

 

 1. የቴክኒክ ስብሰባ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡ዐዐ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይሆናል፡፡
 2. በስብሰባ ላይ የሚገኙት አንድ ቡድን መሪና አንድ አሠልጣኝ ብቻ ይሆናሉ፡፡

 

አንቀጽ አስራ ሰባት

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቡድን ኮታ

 

 1. የትግራይ ክልል 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 2. የአማራ ክልል 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 3. የኦሮሚያ ክልል 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 4. የደቡብ ክልል 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 5. የአዲስ አበባ አስተዳደር 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤

ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች ከተሰጠው ኮታ ውጪ ተጨማሪ የሰው ኃይል የሚያሳትፉ ከሆነ በራሳቸው  ወጪ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

7ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች

መመዝገቢያ ቅጽ

 

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ክለብ/ተቋም ________________________________

 

ተ.ቁ. ሴቶች ተ.ቁ. ወንዶች
የአትሌቷ ስም የአትሌቱ ስም
1.   1.  
2.   2.  
3.   3.  
4.   4.  
5.   5.  
6.   6.  
7.   7.  
8.   8.  
9.   9.  
10.   10.  
11.   11.  
12.   12.  

 

ቅጹን የሞላው

ስምና ፊርማ ___________________

ኃላፊነት __________________

ቀን ____________________

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የ37ኛው ሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ኘሮግራም

 

ቀን፡- 6/10/2013 ዓ.ም.

ቦታ፡- አዲስ አበባ

 

 

ሰዓት ክንውን አፈፃፀም
12፡30 የውድድሩ ስፍራ ለተመልካች ክፍት ይሆናል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ  ፌዴሬሽን
1፡00 የሴቶች ስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
1፡15 የወንዶች ስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
1፡30 የሴቶች/የቬትራን/ ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
1፡45 የወንዶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
4፡30 የሴቶች የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
4፡45 የቬትራን የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
5፡00 የወንዶች የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
5፡15 ለተሳትፎ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
5፡25 የዕለቱን ውድድር አስመልክቶ አጭር መልዕክት ይተላለፋል በኢ.አ.ፌ ፕሬዝዳንት/በእለቱ የክብር እንግዳ
5፡30 የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
5፡40 የውድድሩ ፍፃሜ ይሆናል በሽልማት ኮሚቴ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Details

Date:
June 3
Time:
8:00 am - 5:00 pm
Event Category: