የአትሌቲክስ ስልጠና
 • በረጅም፤ መካከለኛና አጭር ጊዜ መርሀ ግብሮች ተይዘው የአትሌቲስ ስፖርት መሰረቱን ሳይለቅ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚደረግ የባለሙያዎችና አትሌቶች ስልጠናን ያጠቃልላል፤

የባለሙያዎች ስልጠና

 • በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የባለሙያዎች ስልጠና የዳኝነትና አሠልጣኝነት ስልጠናዎች ዋናውን ቦታ ሲይዙ የህክምናና የማሳጅ ስልጠናዎችም ይሰጣሉ፤ በዚህ መሠረት በየደረጃው የሚሰጡ የዳኝነትና አሠልጣኝነት ስልጠናዎችን የስልጠና መግቢያ መስፈርቶችን እንዲሁም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ቁጥር ከዚህ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡
 1. የአሠልጣኝነት ስልጠናዎች
 • 1ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ አሠልጣኝነት ስልጠና
 • 2ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ አሠልጣኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level I አሠልጣኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level II አሠልጣኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level III (Specialization) አሠልጣኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level IV (Senior coach)አሠልጣኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level V (Academy coach)አሠልጣኝነት ስልጠና

 

 • 1ኛ ደረጀ የሀገር ውስጥ አሠልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና ክልሎች ከተማ አስተዳደሮች በራሳቸው ባለሙያና በጀት የሚሰጡት ሰልጠና ሲሆን ስልጠናውን የወሰዱ ባለሙያዎች      በክልላቸው ወይም በሚገኙበት ከተማ ደስተዳደር የማሰልጠኛ ኘሮጄክት ላይ በአሰልጣኝነት ይሰራሉ፤

 • 2ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ አሠልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚሰጥ ሲሆን ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ሰልጣኞችን ያቀርባሉ ስልጠናውን የወሰዱና ያለፋ አሠልጣኞች በክልላቸው/ከተማ አስተዳደራቸው በሚገኙ ማሰልጠኛ ኘሮጄክቶች ማዕከል እንዲሁም ክለቦች ውስጥ በአሠልጣኝነት ያገለግላሉ፡፡

 • የIAAF አንደኛ ደረጃ አሠልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር /IAAF/ ከአባላት ሀገራት ጋር መተባበር የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን ይህንን ስልጠና የወሰዱና ያለፉ አሠልጣኞች በክለቦች ውስጥ በአሰልጣኝነት እንዲሁም እንደየ ስራ ልምዳቸው ብዛት እስከ ምክትል ዋና አሠልጣኝ በመሆን ማገልገል ይችላሉ፤

 • የIAAF ሁለተኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር /IAAF/ ከአባላት ሀገራት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን ይህንን ስልጠና የወሰዱና ያለፉ አሰልጣኞች በክለቦች ውስጥ በአሰልጣኝነት በምክትል ዋና አሰልጣኝነት እንዲሁም እንደየስራ ልምዳቸው ብዛት ዋና አሠልጣኝ በመሆን ማገልገል ይችላሉ፤

 • IAAF ሶስተኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽች ማህበር (IAAF) ከአባላት ሀገራት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን በአመዛኙ በሁለተኛ ደረጃ ስልጠና የላቀ ውጤት ያላቸው አሰልጣኞችን በመምረጥ በ…….በሚሰጠው የሶስተኛ ደረጃ ስልጠና ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በዚህ ስልጠና የተሻለ አፈጻጸም ያገኙ አሰልጣኞች በክለባቸው አሰልጣኝ ፤ም/ዋና አሰልጣኝ፤ ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሆን እድሉን ያገኛሉ፡፡

 • IAAF አራተኛና አምስተኛ ደረጃ አሰልጣኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽች ማህበር (IAAF) ከአባላት ሀገራት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን በየደረጃው በተሰጡ ስልጠናዎች የላቀ ውጤት ያላቸው አሰልጣኞችን በመምረጥ በ..በሚሰጠው ስልጠና ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በዚህ ስልጠና የተሻለ አፈጻጸም ያገኙ አሰልጣኞች በክለባቸው ዋና አሰልጣኝ ወይም ዳይሬክተር የመሆን እድሉን ያገኛሉ፡፡

 1. የዳኝነት ስልጠናዎች
 • 1ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ ዳኝነት ስልጠና
 • 2ኛ ደረጀ የሀገር ውስጥ ዳኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level I (National technical officials)ዳኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level II (Area technical officials) ዳኝነት ስልጠና
 • የIAAF Level III (International technical officials)ዳኝነት ስልጠና
 • 1ኛ ደረጀ የሀገር ውስጥ ዳኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በራሳቸው ባለሙያና በጀት የሚሰጡት ስልጠና ሲሆን ስልጠናውን የወሰዱና ያለፉ ባለሙያዎች በክልላቸው ወይም በሚገኙበት ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ዞኖች ወይም ወረዳዎች በሚደረጉ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ያገለግላሉ፤

 • 2ኛ ደረጃ የሀገር ውስጥ ዳኝነት ስልጠና

ይህ ስልጠና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚሰጥ ሲሆን ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ሰልጣኞችን ያቀርባሉ ስልጠናውን የወሰዱና ያለፋ ዳኞች በክልላቸው/ከተማ አስተዳደራቸው  በሚደረጉ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ያገለግላሉ፤

 • የIAAF አንደኛ ደረጃ ዳኝነት (NTO) ስልጠና

ይህ ስልጠና የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር /IAAF/ ከአባላት ሀገራት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን ይህንን ስልጠና የወሰዱና ያለፉ ዳኞች በሀገር ውስጥ በሚደረጉ ሀገራዊና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ያገለግላሉ፤

 • የIAAF ሁለተኛ ደረጃ ዳኝነት(ATO) ስልጠና

ይህ ስልጠና የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በ/RDC/ የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን ይህንን ስልጠና የወሰዱና ያለፉ ዳኞች በአህጉር ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ያገለግላሉ፤

 • IAAF ሶስተኛ ደረጃ ዳኝነት (ITO) ስልጠና

ይህ ስልጠና የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽች ማህበር (IAAF) በ/RDC/ የሚያዘጋጀው ስልጠና ሲሆን በአመዛኙ በሁለተኛ ደረጃ ስልጠና የላቀ ውጤት ያላቸውና በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ የላቀ አፈጻጸም ያላቸው ዳኞችን በመምረጥ በሚሰጠው የሶስተኛ ደረጃ ስልጠና ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በዚህ ስልጠና የተሻለ አፈጻጸም ያገኙ ዳኞች  በአህጉርና በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውድድሮች ላይ በዳኝነት ያገለግላሉ፤

 

እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ በፌዴሬሽኑ የተሰጡ የሃገር ውስጥና የውጭሃገር የባለሙያዎች

(የዳኝነትና የአሰልጣኝነት) ሰልጣኞች ብዛት፤

ተ.ቁ የስልጠናዓይነት የስልጠናደረጃ የባለሙያዎችብዛት ምርመራ
ድምር
1 አሠልጣኞች 1ኛ ደረጃ የሀገርውስጥ 1139 156 1295
2ኛ ደረጃ የሀገርውስጥ 427 54 481
IAAF I 89 21 110
IAAF II 85 31 116
IAAF III 21 2 23
IAAF IV
ሌክቸረር 2 2 4
2 ዳኝነት 1ኛ ደረጃ የሀገርውስጥ 883 130 1013
2ኛ ደረጃ የሀገርውስጥ 391 78 469
IAAF I 102 20 122
IAAF II 3 2 5