አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የካቲት 15/2010 ኣ. ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በ35ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ዙሪያ ሁሉም የስፖርት ጋዜጠኞች በተገኙበት በኢትዮጵያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያም ውድድሩ የካቲት 18/2010 ዓ. ም. ከማለዳው 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ – ጃን ሜዳ 35ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድርን ያካሄዳል፡፡ በሁሉም ክንውኖች የስፖርት ሚዲያ አካላት በስፍራው በመገኘት መረጃዎቹን መከታተልና ለስፖርት ቤተሰቡ እንዲያደርሱም ፌዴሬሽኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡  በተጨማሪም ከማለዳው 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በዋልታ ቴሌቪዥን በቀጥታ የሚተላለፍ በመሆኑ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ እንዲከታተለው ተጋብዟል፡፡

Similar Posts
Latest Posts from