አትሌት ኃይሌ ቶለሳ ቤኩማ አበረታች መድሃኒት ተጠቅሞ መገኘቱ ስለተረጋገጠ የ4 አመት እገዳ ተጣለበት፤

አትሌቱ ሰሞኑን ይፋ በተደረገ እወጃ መሰረት ከማንኛውም አገራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ የአትሌቲክስ ውድድሮች ለ4 አመት መታገዱ ተገልጧል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሰራርና መመሪያ መሰረት ደግሞ 4 አመት የታገደ አትሌት ምን ሊቀጣ እንደሚችል የተደነገገ ድንጋጌ መኖሩ ይታወቃል፡፡ 
ይሁንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዶፒንግ ጉዳይ ላይ ያለው አቋም ጥብቅ ከመሆኑ አንጻር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በዚህ ጉዳይ ላይ ከመመሪያ አኳያ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ አርብ ጥር 4/2010 ዓ. ም. አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል፡፡

,
Similar Posts
Latest Posts from