የአትሌቲክስ ልኡካን ቡድናችን አሸኛኘት ተደረገ፣
ለ22ኛ ጊዜ በሞሪሽየስ በሚካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው የአትሌቲክስ የልዑካን ቡድን ዛሬ እሁድ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ስርአት ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በተካሄደ መርኃ ግብር በአራራት ሆቴል ተሸኝቷል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት በባህልና ስፖርት ሚ/ር የስፖርት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ፣ የባህልና ቋንቋ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ፣ የኪነጥበብ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃዲ፣ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፣ የኢአፌ ሥራ አስፈፃሚና ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የስፖርት ሚድያ አካላት በሽኝቱ ላይ ተገኝተዋል።
ቡድኑ የአንድ ወር የሆቴል ቆይታውን በተመለከተ አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና የቴክኒክ ቡድን መሪው አቶ አሰፋ በቀለ በየተራ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በፕሮግራሙ መሠረት ለቡድኑ ተወካዮች የሃገር መለያና ምልክት የሆነውን ሰንደቅ አላማ ከታላቅ አደራ ጋር ከክብር እንግዶችና ከፌዴሬሽኑ አመራሮች እጅ ተረክበዋል።
በመጨረሻም ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት በየተራ ባሰሙት ንግግር የሥራ መመሪያና የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል።
Similar Posts
Latest Posts from