አንጋፋውና እድሜ ጠገቡ 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመዝጊው ሥነ ስርዓት በከፍተኛ ድምቀት ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም በሲዳማ ክልል – ሐዋሳ አለም አቀፍ ስቴድዮም የተከናወነ ሲሆን በአጠቃላይ ውጤቱ መሠረት:-
 
🏆 በሴቶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣
1ኛ መከላከያ (መቻል) አት/ቡድን፣ በ192 ነጥብ የዋንጫና የ18,000 ብር ተሸላሚ፣
2ኛ ኢት/ን/ባንክ፣ በ136 ነጥብ፣ የ12,000 ብር ተሸላሚ፣
3ኛ ኢት/ኤሌትሪክ፣ በ89 ነጥብ፣ የ8,000 ብር ተሸላሚ፣
 
🏆በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣
1ኛ ኦሮ/ክልል፣ በ148 ነጥብ፣ የዋንጫና የ18,000 ብር ተሸላሚ፣
2ኛ ኢት/ን/ባንክ፣ በ139 ነጥብ፣ የ12,000 ብር ተሸላሚ፣
3ኛ መከላከያ፣ በ120 ነጥብ፣ የ8,000 ብር ተሸላሚ፣
 
🏆በሁለቱም ፆታ አጠቃላይ አሸናፊዎች፣
1ኛ መከላከያ (መቻል) አትሌ/ቡድን፣ በ312 ነጥብ፣ የዋንጫና የ22,000 ብር ተሸላሚ፣
2ኛ ኢት/ን/ባንክ፣ በ275 ነጥብ የ17,000 ብር ተሸላሚ፣
3ኛ ኦሮሚያ ክልል፣ 235 ነጥብ፣ የ12,000 ብር ተሸላሚ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
 
#ሃዋሳ ስታድየም
Similar Posts
Latest Posts from