ከየካቲት19-24/2014 ዓ.ም በሲዳማ ክልል – ሐዋሳ አለም አቀፍ ስቴድዮም

በተደረገው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አዲስ ሪከርድ ያስመዘገቡ አትሌቶች

 

👉 በጦር ውርወራ ወንዶች በ2013 ዓ.ም. በመከላከያው አትሌት ኡታኔ ኦባንግ 72.40 ሜትር በመወርወር ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የመከላከያው አትሌት ኡተጌ ኦባንግ 73.28 ሜትር በመወርወር የራሱን ተይዞ የነበረውን ሪከርድ አሻሽሏል፡፡
👉 በሴቶች እርምጃ 20 ኪ.ሜ ውድድር በ2009 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አትሌት የኋልዬ በለጠው 1.32፡39 በመግባት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አትሌት የኋልዮ በለጠው 1፡25.50.2 በመግባት የራሷን ሪከርድ አሻሽላለች፡፡
👉 በወንዶች እርምጃ 20 ኪ.ሜ ውድድር በ1998 ዓ.ም. በመከላከያ አትሌት ቸርነት ሚቆሮ 1፡25.28 በመግባት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አትሌት ዮሐንስ አልጋው 1፡17.09.3 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡
👉 በወንዶች 400 ሜ መሠ. በ2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌት ደረሰ ተስፋዬ 50.95 በመግባት ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የመከላከያው አትሌት የውብሰን ብሩ 50.44 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡
👉ወንዶች 3000 ሜትር መሠናክል በ2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ አትሌት ጌትነት የትዋለ 08፡28.98 በመግባት ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የጥሩነሽ ዲባባው አትሌት ሣሙኤል ፍሬው 08፡22.48 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡
👉በወንዶች 3000 ሜትር መሠናክል በ2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ አትሌት ጌትነት የትዋለ 08፡28.98 በመግባት ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የጥሩነሽ ዲባባው አትሌት ሣሙኤል ፍሬው 08፡22.48 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡
👉 በሴቶች 100 ሜትር መሠ. በ2007 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አትሌት ቆንጅት ተመ 14.19 በመግባት ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በኦሮሚያ ክልል አትሌት ሂርጶ ድሪባ 14.08 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆናለች፡፡
👉በወንዶች ዲስከስ ውራወራ በ2004 ዓ.ም. በመከላከያ አትሌት ምትኩ ጥላሁን 44.33 ሜትር በመወርወር ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሲዳማ ቡና አትሌት ማሙሽ ታዬ 45.09 በመወርወር የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡
👉 በ10,000 ሜትር በ1996 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አትሌት ስለሺ ስህን 28፡16.23 በመግባት የተያዘውን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የደቡብ ፖሊስ አትሌት ታደሰ ወርቁ 28፡11.92 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆኗል፡፡
👉 በ10,000 ሜትር በ2011 የትራንስ ኢትዮጵያ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 32፡10.13 በመግባት የተያዘውን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አትሌት ግርማዊት ገ/እግዛብሔር 31፡21.48 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆናለች፡፡
👉 በሴቶች ዲስከስ ውርወራ በ2013 ዓ.ም. በኢት/ንግድ ባንክ አትሌት መርሃዊ ፀሀዬ 42.87 በመወርወር የተያዘው ሪከርድ በ51ኛው የኢት/አት/ሻምፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌት መርሃዊት ፀሐዬ 45.40 በመወርወር የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆናለች፡፡
👉 በሴቶች 100 ሜትር ውድድር በ1998 በኢት/ንግድ ባንክ አትሌት አታክልቲ ውብሸት 11፡55 በመግባት ተይዞ የነበረው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻንፒዮና ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያብስራ ጃርሶ 11፡46 በመግባት የአዲስ ሪከርድ ባለቤት ሆናለች፡፡
👉 አሎሎ ውርወራ ውድድር በ2011 ዓ.ም. በመከላከያ አትሌት ዙርጋ ኡስማን 13.55 ተወርውሮ የተያዘው ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ላይ የመከላከያ አትሌት የሆነችው አትሌት ዙረጋ ኡስማን 13.56 በመወርወር የራሷን ሪከርድ አሻሽላለች፡፡
👉 በስሉስ ዝላይ ውድድር በ2011 ዓ.ም. በመከላከያ አትሌት አዲር ጉር 15.88 በመዝለል ተይዞ የነበረዉን ሪከርድ በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አትሌት ክችማን ኦጅሉ 16.03 በመዝለል የአዲስ ሪከረድ ባለቤት ሆኗል፡፡
 
#ሃዋሳ ስታድየም
Similar Posts
Latest Posts from