10ኛው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች እና 3ኛው ከ18 አመት በታች የአትሌተቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሰኞ የካቲት 28/2014 ዓ.ም ከቀነ 7:00 ላይ በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ አረንጓዴው ስቴድዮም በክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የመክፈቻ ንግግር በይፋ ተጀምሯል።
ይህ ውድድር ለተተኪ አትሌቶች የውድድር እድል ከመፍጠሩም በላይ በቅርቡ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ለሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ ታዳጊና ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች የሚመረጡበት መሆኑም ተገልጿል።
የውድድሩ መክፈቻ የተደረጉት ውድድሮች የሴቶች ጦር ውርወራ ከ20 አመት በታችፍፃሜ፣ የወንዶች ከፍታ ዝላይ ከ20 አመት በታች ፍፃሜ፣ እንዲሁም የሴቶች ከ18 አመት በታች 800 ሜ ማጣሪያ ናቸው።
 
በመጀመሪያው ቀን የታዳጊዎችና ወጣቶች ውድድር በጦር ውርወራ ሴት አሸናፊዎች ከ20 አመት በታች፣
1ኛ ድንገቴ ሆቶላ ኦሮሚያ ክልል 51.46 ሜ
2ኛ ታደለች ቶንቶ ከሲዳማ ቡና 47.52 ሜ
3ኛ የሺወርቅ አንማው ከኢት/ን/ባንክ 46.22 ሜ
 
በ5000 ሜ ሴቶች ከ20 አመት በታች፣
1ኛ መልክናት ውዱ ኢት/ን/ባንክ 16:02:60
2ኛ አሳየች አይቼው ከአማራ ክልል 16:02:91
3ኛ በቀለች ተኩ ከኦሮሚያ ክልል 16:06:65 በሆነ ጊዜ አሸናፊዎች ሆነዋል።
 
ከ20 አመት በታች ወንዶች ከፍታ ዝላይ አሸናፊዎች፣
1ኛ ዱፕ ሌም ከሲዳማ ቡና 2.10 ሜ
2ኛ ኡጁሉ አንበሴ ኢት/ኤሌክትሪክ 2.05 ሜ
2ኛ ቦይ ጋልዋክ ኦሮሚያ ክልል 2.05 ሜ
Similar Posts
Latest Posts from