የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፤
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት በተለያዩ የሃገራችንን ክልሎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በከፋ ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች በዛሬው እለት ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡
ድጋፉ የተደረገላቸው ክልሎች የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ሁለት ሚሊዮን ብር፣ የሶማሌ ብሔራዊ ክልል አንድ ሚሊዮን ብር፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል አንድ ሚሊዮን ብር በድምሩ አራት ሚሊዮን ብር ሲሆን ድጋፉንም ከኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ከኢ.አ.ፌ. ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እጅ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር የኦሮሚያ ብ/ክልል መንግስት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራርና የልማት ተነሺ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ መሀመድ መሃዲ የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና አቶ ተፈራ ሞላ የደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች ክልል ተወካይ በፌዴሬሽኑ ተገኝተው ድጋፉን ተረክበዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ክልል ተወካዮችም ለተደረገላቸው ድጋፍ በክልላቸው ስም በማመስገን የተደረገውን ድጋፍ በአግባቡ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚሆን ገልፃዋል፡
 
Similar Posts
Latest Posts from