በሃዋሳ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 25ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በ2013 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ክለቦች እውቅናና ሽልማት የሰጠ ሲሆን በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግራቸው በሁለት ቀናቱ የጉባኤው ውሎ በርካታና ጠቃሚ ውይይቶችን በማድረግ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔዎችን ወደ መሬት አውርዶ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ሚኒስትር መስሪያ ቤታቸው ስፖርቱን እድገት ለማሳደግ በጋራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያም የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል። ጉባኤውም በዚሁ መዝጊያ ንግግር ፍፃሜውን አግኝቷል።

Similar Posts
Latest Posts from