አዲዳስ ኤዲዜሮ የ5ኪሜ የጎዳና ውድድር አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የዓለም ሪከርድን ሰበረች፤
 
አዲዳስ የስፖርት ትጥቆች አምራች ኩባንያ በጀርመን ሄርዞጌናውሪች በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ አዲዜሮ በሚል ስያሜ የጎዳና ላይ ውድድር ፌስቲቫል ላይ በ5ኪሜ የሴቶች የጎዳና ሩጫ የተሳተፈችው አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ14:29 በሆነ ሰዓት የዓለም የርቀቱን ሪከርድ ጭምር በመስበር አሸንፋለች በዚህ ውድድር ላይ የተካፈሉት መልክናት ውዱና ንግስቲ ሀፍቱ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ በወንዶች 10 ኪሜ ውድድር አትሌት ታደሰ ወርቁ በ26:56 በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
 
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለም አገራት በተካሄዱ የጎዳና ሩጫ ላይ
የተሳተፉ የሃገራችን አትሌቶች ያስመዘገቧቸው ውጤቶች፡-
 
በኦስትሪያ፣ ቬይና ማራቶን
በወንዶች
2ኛ በተስፋ ጌታሁን በ2:09:42
በዚሁ ውድድር ላይ ተሳትፎ በአንደኝነት አጠናቆ የነበረው አትሌት ደራራ ሁሪሳ ባልተፈቀደ ጫማ በመሮጡ ያገኘው ደረጃና ውጤት ተሰርዞበታል፡፡ ወጤቱን ያሰረዘበት ጫማ የሶል ውፍረት ከ40 ሚሊ ሜትር በላይ በመሆኑ ነበር፡፡
በሴቶች
2ኛ መሰረት ድንቄ በ2:25:31
3ኛ ገለቴ ቡርቃ በ2:25:38
በጀርመን፣ ሃምቡርግ ማራቶን
በወንዶች
2ኛ ማስረሻ ቢሰጠኝ በ2:10:55
3ኛ በላይ በዛብህ በ2:14:01
5ኛ ደረሰ ካሴ በ2:17:38
በሴቶች
1ኛ ጋዲሴ ሙሉ በ2:26:19
በጀርመን፣ ሄርዞገናውራች ኤዲ ዜሮ የጎዳና ላይ ፌስቲቫል ውድድር
በግማሽ ማራቶን ውድድር
በወንዶች
8ኛ ዳኛቸው አደሬ በ1:02:05
9ኛ ሃይማኖት ማተብ በ1:03:10
11ኛ ግርማ በቀለ በ1:05:59
በሴቶች
2ኛ በሱ ሳዶ በ1:08:15
4ኛ ፅጌ ኃ/ስላሴ በ1:08:30
8ኛ ብርሆ አድሃና በ1:09:42
በ10 ኪሎ ሜትር ውድድር
በወንዶች
2ኛ ታደሰ ወርቁ በ26:56
5ኛ ባየልኝ ተሻገር በ27:24
8ኛ ሞገስ ጥኡማይ በ27:50
በሴቶች
7ኛ ሶፊያ ሸምሱ በ32:24
9ኛ አለምአዲስ እያዩ በ33:20
በ5 ኪሎ ሜትር ውድድር
በወንዶች
2ኛ ሙክታር ኢድሪስ በ13:09
በሴቶች
1ኛ ሰንበሬ ተፈሪ በ14:29 በሆነ ሰዓት የዓለም ሪከርድን ጭምር በመስበር
2ኛ መልክናት ውዱ በ14:54
3ኛ ንግስቲ ሃፍቱ በ14:54
5ኛ ዳዊት ስዩም በ15:10
6ኛ መዲና ኢሳ በ15:13
7ኛ አለሚቱ ታሪኩ በ15:15
12ኛ መቅደስ አበበ በ15:56
በደቡብ አፍሪካ፣ ደርባን የሴቶች ስፓና ግራንድ ፕሪክስ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር
1ኛ ታዱ ናሪ በ32:07
በስዊዲን፣ ጉተንበርግ ግማሽ ማራቶን
በወንዶች
2ኛ ከበደ ዋሚ በ1:01:12
በሴቶች
9ኛ ወይንሸት አንሳ በ1:14:03
10ኛ አዲስዓለም በላይ በ1:14:09
በፈረንሳይ ዱ ፔይ ኢን
ቬሊ 15 ኪሎ ሜትር ውድድር
በወንዶች
8ኛ ሲሳይ ያዘው በ48:06
በሴቶች
3ኛ ልቅና አምባው በ52:09
5ኛ ገነት አብዱልቃድር በ54:18 በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
አትሌቶቻችን እና አሰልጣኞቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
ምንጭ፡- የአፍሪካ አትሌቲክሰ ዩናይትድ የማህበራዊ ትስስር ገፅ
 
 
 
 
Similar Posts
Latest Posts from