በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታችአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ በአስራ ሁለት ሜዳልያዎች አራተኛ ደረጃ ከዓለም በመያዝ ያጠናቀቀው ልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክ/ፕሬዝዳንት የተከበሩ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ የተመራ የፌዴሬሽናችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለቡድኑ ጉንጉን አበባ በማበርከት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል። አትሌት መሰለች መልካሙ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ም/ፕሬዝዳንትም በማህበሩ ስም ለልኡኩ ጉንጉን አበባ አበርክታለች።
የተከበሩ ወ/ሮ አበባ በቡድኑ ለተመዘገበው ውጤት እጅግ መኩራታቸውን ገልፀው እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን በድል ተመለሳችሁ በማለት በንግግራቸው ገልፀዋል።
Similar Posts
Latest Posts from