በኬኒያ-ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና  በወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ታደሰ ወርቁ በ13:20.65 በሆነ ሰዓት 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ሲያሸንፍ ሌላኛው አትሌት አዲሱ ይሁኔ በ13:32.76 በሆነ ሰዓት 4ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ ዲፕሎማ አግኝቷል።
 
የሴቶች 3000 ሜትር ውድድር ሃገራችንን በብቸኝነት የወከለችው አትሌት መልክናት ውዱ በ9:00.12 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ ሶስተኛ በመውጣት የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።
እንኳን ደስ አለን!
Similar Posts
Latest Posts from