የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጋር በመተባበር ለአትሌቲክስ ስፖርት አሰልጣኞች፣ ለአትሌት ተወካዮችና ለህክምና ባለሙያዎች በልዩ ልዩ ጤና ነክ የአትሌቲክስ ስፖርት ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ ጥቅምት 27/2010 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢ.ፌዲሪ ወ/ስ/ሚ/ር አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ በንግግር ከፍተውታል።

ሥልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ዶ/ር ስቴፈን ቤርሞን በIAAF የህክምናና ሣይንሣዊ ጥናቶች ከፍተኛ አማካሪ ሲሆኑ የሥልጠናው ትኩረት፦
– በሴት አትሌቶች ተፈጥሯዊ ክስተትና የሥልጠናና ውድድር መገጣጠም፣

– በደም ውሥጥ የIron ማእድን እጥረት፣

– በአትሌቲክስ ሥልጠናና ውድድር የሚያጋጥሙ ጉዳቶች፣

– የአትሌቲክስ አሰልጣኞችና ተወካዮቻቸው ዶፒንግ በመከላከል ላይ ያላቸው ሚና በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

Similar Posts
Latest Posts from