በኬንያ – ናይሮቢ የሚካሄደውንና ኢትዮጵያ የምታካፈልበትን 18ው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (ወጣቶች) አትሌቲክስ ሻምፒዮናን አስመልክቶ  ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሺኝት መርሀ ግብር ተከናወነ   – ነሐሴ 8/2013 ዓ.ም.

ለገጣፎ-ለገዳዲ በሚገኘው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል ከአንድ ወር በላይ ስልጠናውን ሲያካሂድ የቆየው የ18ው የዓለም ከ20 ዓመት በታች(ወጣቶች) አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን  ዛሬ ቅዳሜ  ነሐሴ 8/2013 ዓ.ም. ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ፕሬዝዳንት፣  አትሌት ገዛኸኝ አበራ  የኢ.አ.ፌ ም/ተ/ፕሬዝዳንትና የቡዱኑ  መሪ፣ የኢ.አ.ፌ. ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና  የኢ.አ.ፌ. ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ  በተገኙበት  አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ደማቅ የሆነ አሽኛኝት ተደርጎለታል፡፡

በሽኝቱ ወቅት የአትሌቶች ተወካዮች አትሌት መልኬነህ እዘዝ (1,500 ሜ) እና አትሌት ንግስት ጌታቸው (4 በ400 ሜ)፣የአሰልጣኞቸ ተወካይ አብዮት ተስፋዬ (መካከለኛ ርቀት)፣ የቡድኑ መሪና የኢአፌ ተቀ/ም/ፕሬዝደንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ስለአጠቃላይ የቡድኑ ዝግጅት አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን ክብርት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት በራሷና በኢአፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስም ለልኡካን ቡድኑ አባላት የመልካም ምኞት መግለጫና አጠቃላይ መመሪያ አስተላልፋለች፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተነሱ ጉዳዮች ኢትዮጵያ በ10 ወንድ፣ በ15 ሴት እና በአጠቃይ በ25 አትሌቶች ከአጭር ርቀት ጀምሮ ወጣቶች በሚሳተፉባቸው የረጅም ርቀቶች፣ በ3000ሜ.መሰናክልና በእርምጃ ውድድሮች እንደምትካፈልና ቡድኑ ለአንድ ወር ያህል ሆቴል ገብቶ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱን፣ ለቡድኑ የሚያስፈልጉ የልምምድና የውድድር ስፖርት ትጥቆች በአግባቡ እንደደረሳቸው አብራርተዋል ፡፡  

ዝርዝር መረጃውን  ቀጥሎ ይመልከቱ፡-

የአለም ከ20 አመት በታች (ወጣቶች) አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአለም አትሌቲክስ አዘጋጅነት እ.ኤ.አ ከ1986 ጀምሮ በየ2 አመቱ ለ5/6 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ የመምና የሜዳ ተግባራትን ያካተተ እና እድሜያቸው ከ20 አመት በታች የሆኑ አትሌቶች የሚወዳደሩበት የአትሌቲክስ ውድድር ነው፡፡ 

ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ በተካሄዱት 17 የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በ37 ወርቅ፣ በ32 ብር፣ በ29 ነሃስ፣ በድምሩ በ98 ሜዳልያዎች ከአለም 5ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ከነዚህ ውስጥ 49ኙ ሜዳልያዎች በሴቶች፣ 47ቱ ደግሞ በወንድ አትሌቶች የተመዘገቡ ናቸው፡፡

ሪከርዶች

  እንደ አትሌት አብርሃም ጨርቆሴ ያሉ ድንቅ ኢትዮጵያዊ አትሌቶች በ5,000 ሜ ወንዶች በ2008፣

  በ3,000 ሜ ሴቶች አትሌት በየኑ ደገፋ በ2016፣

  በ5,000 ሜ ሴቶች አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ2010 ውድድር እስከዛሬ የሪከርዱ ባለቤቶች ናቸው፡፡

ድርብ ድሎች

ሻምፒዮናው ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ 14 አትሌቶች በአንድ ሻምፒዮና የድርብ ድል ባለቤቶች ነበሩ፡፡ ለአብነት ለመጥቀስም፡-

  ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በ5 እና 10 ሺህ ሜ. እ.ኤ.አ በ1992፣

  አትሌት አሰፋ መዝገቡ በ5 እና 10 ሺህ ሜ እ.ኤ.አ በ1996፣ እንዲሁም

  ጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋር በ3 እና 5 ሺህ ሜ. እ.ኤ.አ በ2002 አሸናፊዎች ነበሩ፡፡

አመርቂ ውጤቶች

  አገራችን በሻምፒዮናው አመርቂ ውጤት ያስመዘገበችው በ6ኛው የአውስትራሊያ – ሲድኒ፣

  በ14ኛው የስፔን – ባርሴሎና  እንዲሁም

  በ16ኛው የፖላንድ – ቢድጎሽ የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ የ17ኛው ከ20 አመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያን ውጤት ለማስታወስ ያክል፡-

በ2018 የ17ኛው ፊንላንድ – ቴምፔር የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ፣

ወርቅ፣

አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ800 ሜ፣

አትሌት አልማዝ ሳሙኤል በ1,500 ሜ፣

አትሌት ታከለ ንጋቴ በ3000 ሜ. መሰ፣

ብር፣

አትሌት መሰሉ በርሄ በ3000 ሜ፣

አትሌት እጅጋዬሁ ታዬ በ5000 ሜ፣

ነሃስ፣

አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ በ3000 ሜ፣

አትሌት ግርማዊት ገረዝሄር በ5000ሜ፣

አትሌት ጌትነት ዋለ በ3000 ሜ መሰ፣

አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10000 ሜ፣

 

በ2021 የኬንያው 18ኛው የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ፡-

  ዘንድሮ እ.ኤ.አ ከኦገስት 17 እስከ 22/2021 በኬንያ ናይሮቢ ከተማ ለ18ኛ ጊዜ ይካሄዳል፤

  የውድድሩ ዓላማ፡- ወጣት አትሌቶቻችን በአለም አደባባይ አገራቸውን በድል ለማስተዋወቅና ለአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ልምድ እንዲቀስሙ ለማስቻል ነው፡፡

  የአትሌቶች ብዛት፡- 15 ሴቶች፣ 10 ወንዶች፣ በድምሩ 25 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ከአጭር ርቀት 400 ሜ ጀምሮ በ8 የውድድር አይነቶች ይካፈላሉ፤

  ስልጠና፡- ፌዴሬሽኑ እነዚህን አትሌቶች ለአንድ ወር ያህል ሆቴል በማስገባት ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፣

  ህክምና፡- በቆይታቸው የልምምድና የውድድር ስፖርት ትጥቆችን አቅርቧል፤ የኮቪድ 19 እና የዶፒንግ ምርመራዎች ተከናውነዋል፤

  የአትሌቶች ዝርዝርና ኢቨንቶች፡-

 

ተ.ቁ   ስም ዝርዝር  ኢቨንት

 1. ዳንኤል ወልዴ 800 m
 2. ኤርማያስ ግርማ 800 m
 3. አያል ዳኛቸው 800 m
 4. መብርሂት መኮንን 800 m
 5. መልኬነህ አዘዘ 1500 m & mixed
 6. ወገኔ አዲሱ 1500 m & mixed
 7. ድርቤ ወልተጂ 1500 m
 8. ህይወት መሃሪ 1500 m
 9. ታደሰ ወርቁ 3000 m
 10. አሊ አብዱልመናን 3000 m
 11. መልክናት ውዱ 3000 m
 12. አዲሱ ይሁኔ 5000 m
 13. መብራቱ ወርቁ 5000 m
 14. ሚዛን አለም 5000 m
 15. መዲና ኢሳ 5000 m
 16. ታደሰ ታከለ 3000 m stc
 17. ሳሙኤል ፍሬው 3000 m stc
 18. ዘርፌ ወንድማገኝ 3000 m stc
 19. እመቤት ከበደ 3000 m stc
 20. መታሰቢያ ወርቁ Race Walk
 21. ውባለም ሽጉጤ Race Walk
 22. አማረች ዛጎ 400 m, 4×400 m
 23. ሃና ታደሰ 400 m, 4×400 m
 24. ንግስት ጌታቸው 400 m, 4×400 m
 25. ምህረት አሻሞ 400 m, 4×400 m

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

መልካም እድል ለአትሌቶችችን!

Similar Posts
Latest Posts from