በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ሃገራችንን የወከለው ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት አቀባበል ተደረገለት፤
ዛሬ ማለዳ ከቶኪዮ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰውና ሃገራችንን የወከለው ልኡክ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በመወከል ተቀ/ም/ፕሬዝዳንቱ አትሌት ገዛኸኝ አበ፣ ምክ/ፕሬዝዳንቷ የተከበሩ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ አቶ ተፈራ ሞላና ኮ/ር አትሌት ማርቆስ ገነቲ ተገኝተዋል።
ለልኡካን ቡድኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በመወከል አትሌት ገዛኸኝ አበራ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበርን በመወከል ኮ/ር አትሌት ማርቆስ ገነቲ ጉንጉን አበባ አበርክተዋል።
Similar Posts
Latest Posts from