በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ሃገራችንን የሚወክለው የልኡካን ቡድን አባላት  በታላቁ ቤተመንግስት ደማቅ አሸኛኘት ተደረገለት
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፕሬዝዳንት ክብርት ሣህለ-ወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ሃገራችን በአትሌቲክሰ፣ በውሃ ዋና፣ በቴኳንዶና በብስክሌት የስፖርት አይነቶች ለሚወክሉ የልኡካን ቡድን አባላት ደማቅ የሆነ የሽኝት መርሃ ግብር ትላንት ምሽት በታላቁ ቤተመንግስት በማካሄድ ለቡድኑ መልካም እድል እንዲገጥመው በመመኘት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከቡድኑ ለተወከሉት አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አስረክበዋል፡፡
በሽኝት መርኃ ግብሩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የተከበሩ አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ፣ የኢአፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በአሸኛኘት መርኃ ግብሩ ወቅትም ክብርት ወ/ሮ ሣህለ-ወርቅ ዘውዴ ለቡድኑ መልካም ምኞታቸውን የሚገልፅ ንግግር አሰምተዋለው፡፡ በመጨረሻም ለቡድኑ አባላትና ለተጋባዥ እንግዶች የእራት መስተንግዶ ተደርጓል፡፡
Similar Posts
Latest Posts from