ሬ ምሽት በካፒታል ሆቴል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስፖንሰር የሆነው ሶፊ ማልት በቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ ሀገራችንን የሚወክለውን የልኡካን ቡድን አባላትን በድል ተመለሱ በሚል የሽኝት እና የእራት መርሀ ግብር በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።
በዚህ የሽኝት ስነ ስርዓት ክብርት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢአፌ ፕሬዝዳንት፣ ሚስተር ሂውበርት የሃይኒከን ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢአፌ የጽ/ቤት ኃላፊና የቶኪዮ ኦሊምፒክ አትሌቲክስ ቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አቶ ፍቃዱ በሻ የሃይኒከን ኢትዮጵያ የውጭ ግኑኝነት ኃላፊ፣ ሚስ ጃክሊን የሃይኒከን ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ማናጀር እና በቶኪዮ 2020 (2021) ሃገራችን በአትሌቲክስ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በሽኝቱ ላይ አቶ ፍቃዱ ባሻ ሶፊ ማልት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የሁል ጊዜም አጋር መሆኑን ገልፀው ለቶኪዮ ኦሊምፒክ አትሌቲክስ ቡድናችን መልካም እድል ተመኝተዋል። በመቀጠልም አቶ ቢልልኝ መቆያ ለሶፊ ማልት ምስጋና አቅርበዋል ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በንግግራቸው ሶፊ ማልት ላዘጋጀው የሽኝት መርሀ ግብርና መልካም ምኞት ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና አቅርበዋል።
Similar Posts
Latest Posts from