በቶኪዮ 2020 (2021) ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤
************************************************
ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 24/2013 ዓ. ም. ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ 2020 (2021) ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ዝግጅትን አስመልክቶ በሂልተን ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ለስፖርት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት፣ ክብርት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የልኡካን ቡድኑ ኦፊሽያል፣ ክብርት አትሌት ብርሃኔ አደሬ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የኢአፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና በቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ቡድኑ መሪ፣ አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢአፌ ጽ/ቤት ኃላፊና በቶኪዮ ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ልኡኩ የቴክኒክ ቡድን መሪ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ የስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች በተገኙበት መግለጫው የተሰጠ ሲሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን በቶኪዮ 2020 (2021) በአትሌቲክሰ ሃገራችንን የሚወክሉ አትሌቶችን፣ አሰልጣኞችንና ኦፊሻሎችን ከተመረጡበት መስፈርት፣ በሆቴል በቆዩባቸው ስምንት ወራት የነበረው የዝግጅት ሂደት፣ ከኮቪድ ፕሮቶኮል አጠባበቅና ተያያዥ ጉዳዮች አንፃር ሲሰራ የነበረውን ተግባር በዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
የጋዜጣዊ መግለጫውን ሙሉ መረጃ ከዚህ በታች አያይዘናል፤ ይመልከቱት፡፡
 
 
 
 
 
 
 
Similar Posts
Latest Posts from