የቶኪዮ 2020 (2021) ኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ቡድናችን ‹‹ኢትዮጵያን እናልብሳት›› በሚለው የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የመርኃ ግብሩ መሪ ቃል መሰረት አረንጓዴ አሻራውን በኢትዮጵያ ወጣ/ስፖ/አካዳሚ አኖረ፤
   ************************************************
 
በጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ‹‹ኢትዮጵያን እናልብሳት›› በሚል የተሰየመውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቶኪዮ ኢሊምፒክ ሃገራችንን በአትሌቲክስ የሚወክለው ቡድናችን፣ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ፣ የማኔጀመንት ኮሚቴ አባላትና ሰራተኞች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተ/አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቢንያም ምሩፅ በተገኙበት ቡድኑ በፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ክብርት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እየተመራ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 23/2013 ዓ. ም. ጠዋት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን ተክሏል፡፡
በመርሃ-ግብሩም ላይ ልኡካን ቡድኑ መልካም እድል ይገጥመው ዘንድ በመመኘት የእለቱ መርኃ ግብር ተጠናቋል፡፡
Similar Posts
Latest Posts from