የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የህፃናት አትሌቲክስ ስልጠና ፓይለት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች አስጀምረዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስብስቴ ነጋሲ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና በየካ ክፍለ ከተማ ደጃ/ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 10/2013 ዓ. ም. ከማለዳው 3፡00 ጀምሮ በደማቅ ሥነ ስርዓት የህፃናት አትሌቲክስ ፓይለት ስልጠና ፕሮግራሙ የተጀመረ ሲሆን የየት/ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን፣ የ2ቱም ክፍለ ከተሞች ስፖርት አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተ/አስ/ስፖርት ኮሚሽን ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩጽ ይፍጠር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ባስተላለፉት መልእክት በአይነቱ ልዩና የመጀመሪያ የሆነው የህፃናት አትሌቲክስ ስልጠና በተመረጡ 2 የአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ለሞዴልነት መጀመሩን አስመልክተው በተለይ አቶ ቢኒያም ምሩጽና አቶ ቢልልኝ መቆያ እያንዳንዱ ፓይለት ፕሮጀክት እድሜያቸው ከ7 – 12 አመት የሆናቸውን 15 ወንዶችና 15 ሴቶች፣ በድምሩ 30 ህፃናትን የሚይዝ ሆኖ በባለሙያ፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብና በሞራል ድጋፍና ክትትል እተደረገ ህፃናቱ በበቂ ልምምድ ውጤታማ የቆይታ ጊዜያቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ታዳጊ ወጣት ፕሮጀክት፣ ከዚያም ወደ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትና ወደ ክለቦች ሊሸጋገሩ የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቶ ኢትዮጵያን የነገ ስመ ጥር ባለድል አትሌቶች መገኛ ለማድረግ፣ ስመ ጥሮቹን አትሌቶች ሊተኩ የሚችሉ ምርጥ እና ውጤታማ ተተኪዎች ከወዲሁ እያፈራን ኢትዮጵያ የማይነጥፍ የውጤታማ አትሌቶች ምንጭ እንድትሆን ሁላችንም በጋራ እንሰራለን ካሉ በኋላ የህፃናት አትሌቲክስ ፓይለት ፕሮግራሙ በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡
በመጨረሻም ህፃናቱ በየእድሜ ደረጃቸው የመስክ የተግባር ልምምድ በማድረግ ስልጠናቸውን ለእለቱ የክብር እንግዶች አሳይተዋል፡፡
 
 
Similar Posts
Latest Posts from