በባህርዳር ሁለገብ ስቴድየም ከሚያዝያ 14-16/2013 ዓ.ም. ሲካሄድ የቆየው 1ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለአሸናፊ ማሰልጠኛ ማዕከላት የዋንጫ ሽልማት በማካሄድ ውድድሩ ተፈፅሟል ።
 
በዚህም መሠረት በሴቶች ምድብ በተደረገው ውድድር አጠቃላይ ድምር
1ኛ ደብረብርሃን አት/ማሰ/ማዕከል በ201.5 ነጥብ የዋንጫ ተሸላሚ
2ኛ ፈረስ ቤት አት/ማሰ/ማዕከል በ130.5 ነጥብ
3ኛ ተንታ አት/ማሰ/ማዕከል በ83.5 ነጥብ
በወንዶች አጠቃላይ ድምር
1ኛ ደብረብርን አት/ማሰ/ማዕከል በ164.5 ነጥብ የዋንጫ ተሸላሚ
2ኛ ተንታ አት/ማሰ/ማዕከል በ154.5 ነጥብ
3ኛ ጂንካ አት/ማሰ/ማዕከል በ120 ነጥብ
በአጠቃላይ በወንዶችና በሴቶች ድምር ውጤት
1ኛ ደብረብርሀን አት/ማሰ/ማዕከል በ336 ነጥብ አሸናፊና የዋንጫ ተሸላሚ
2ኛ ተንታ አት/ማሰ/ማዕከል በ238 ነጥብ
3ኛ ጂንካ አት/ማሰ/ማዕከል በ192
ነጥብ በማምጣት ውድድሩ ሲጠናቀቅ በዕለቱ በስፍራው በመገኘት የዋንጫ ሽልማት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ፣ ዶ/ር ዘላለም መልካሙ የአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እጅ ለአሸናፊዎች ተሰጥቶ 1ኛው የኢትዮጵያ ማሠልጠኛ ማዕከላት ሻምፒዮና ተጠናቋል። በሻምፒዮናው በሁሉም የውድድር ተግባራት ከ1ኛ-3ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች ከሜዳልያ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፌዴሬሽኑ በአጠቃላይ ለሽልማት አንድ መቶ ሺ ብር ወጭ አድርጓል።
Similar Posts
Latest Posts from