የ50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በተሳታፊ ቡድኖች የሰልፍ ትርኢት በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ ማርች ባንድ ታጅቦ መክፈቻው በድምቀት የተካሄደ ሲሆን በመቀጠልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሻምፒዮናውን አስመልክቶ ንግግር አድርገው የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ኤልያስ ሽኩር ሻምፒዮናውን በይፋ ከፍተዋል።

የ10000 ሜትር የወንዶች ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል በውጤቱም:-

1ኛ በሪሁ አረጋዊ ከኦሊምፒክ ቡድን
2ኛ ሀጎስ ገ/ህይወት ከኦሊምፒክ ቡድን
3ኛ ታዬ ግርማ ከኦሮ/ደንና ዱር እንስሳት
4ኛ ዮሚፍ ቀጄልቻ ከኦሮሚያ ክልል
5ኛ ታደሰ ወርቁ ከደቡብ ፖሊስ
6ኛ ጫላ ከተማ ከአሮ/ ውሃ ስራዎች

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Similar Posts
Latest Posts from