ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከየካቲት 23 – 28/2013 ዓ ም በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት አሰላ ከተማ አረንጓዴው ስቴድዮም ሲካሄድ ሰንብቶ ዛሬ በደማቅ ሥነ ስርአት ተጠናቋል::
በመዝጊያ ሥነ ስርአቱ ላይ ክቡር አቶ ናስር ሁሴን የኦሮ/ክልል ስፖርት ኮ/ኮሚሽነር፣ የተከበሩ አቶ ወርዶፋ በቀለ የህ/ተ/ም/ቤት አባልና የኦሮ/ክል አትሌቲክስ ፌዴ/ፕሬዝዳንት፣ አቶ መዘረዲን ሁሴን የደቡብ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ የኢአፌ ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት፣ አቶ ሺመልስ አሳኑ የኦሮ/አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክ/ፕሬዝዳንት ተገኝተው ለአሸናፊዎች ሽልማቶችን አስረክበዋል።
በአጠቃላይ ውጤት እና በሴቶችም በወንዶችም የኦሮሚያ ክልል የተዘጋጁትን 3 ዋንጫዎች በበላይነት አሸንፎ መውሰድ ችሏል።

Similar Posts
Latest Posts from