የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት የድል በዓልን አስመልክቶ የሩጫ ውድድር ዛሬ እሁድ የካቲት 21/2013 ዓም ከማለዳው 2:00 ጀምሮ በጋራ አካሂደዋል፣
የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሩ መነሻውንና መድረሻውን መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ አድርጎ ተካሂዷል።
በዚህ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የአትሌቲክስ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ አንጋፋ አትሌቶች፣ የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በውድድሩ የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት “አድዋ የህብረ ብሄራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል 5 ኪሜ ውድድሩን ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ክብርት ወ/ሮ ፈሪሀ መሀመድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚኒስቴር ዴአታ ማዕረግ አማካሪ፣ ክብርት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የኢአፌ ፕሬዝዳንት እና አትሌት ገዛኸኝ አበራ የኢአፌ ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት በቦታው በመገኘት አስጀምረዋል።
ውድድሩን በሴቶች
1ኛ ኩሜ ግርማ
2ኛ ገዳምነሽ መኳንንት
3ኛ ጫልቱ ፍቃዱ
በወንዶች
1ኛ ቹቹ አበበ
2ኛ ሀብታሙ ከበደ
3ኛ ናኦል ገመቹ ሲያሸንፋ ሜዳልያና ሰርተፍኬት ከእለቱ የክብር እንግዶች ተቀብለዋል።
በመጨረሻም ክብርት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ እና ክብረት ዶ/ር ሂሩት ካሰው በየተራ ባስተላለፉት መልእክትና መዝጊያ ንግግር የአድዋ ድል የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ በመሆኑ በዛሬው እለት በጎዳና ሩጫ ስናከብረው ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
በማያያዝም ውድድሩ በፌዴሬሽኑ አመታዊ የውድድር እቅድ ውስጥ ተካትቶ በየአመቱ እንደሚካሄድ ኮ/ር ደራርቱ አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ ተካሄደ
 
 
 
 
 
 
 
 
Similar Posts
Latest Posts from