በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በአትሌቲክስ መነቃቃት ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ጉዞ ተደረገ:-
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢአፌ የጽ/ቤት ኃላፊ የተመራ የልኡካን ቡድን አባላት ከሐሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በሱማሌ ክልል፣ በሀረሪ ክልል እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ከየክልሎቹና ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በስፖርቱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ አትሌቶች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገው ሲሆን የአትሌቲክሱን እንቅስቃሴ ይበልጥ አጎልብቶ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።
በክልሎቹና ከተማ አስተዳደሩ በአትሌቲክ ስፖርት ትኩረት ሰጥቶ ከመስራት ባለፈ አትሌቲክስ ለሃገራው ህብረ ብሄራዊ አንድነት ሚናው የጎላ በመሆኑ የበለጠ መስራት እንደሚገባ ስምምነት ተደርሷል። በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ያለውን የአትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና ተተኪዎ ለማፍራት ለሚሰራው ስራ አቅም በፈቀደ መጠን በቴክኒክ፣ በአቅም ግንባታና፣ በማቴሪያል ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
Similar Posts
Latest Posts from