የፊታችን እሁድ የካቲት 14/2013 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ የሚካሄደውን 14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድርን አስመልክቶ ዛሬ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ራስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን በመግለጫው ኮ/ር ማርቆስ ገነት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት፣ አቶ አስፋው ዳኜ የተሳትፎና ውድድር ንኡስ የስራ ሂደት መሪ፣ ኮ/ር ብርሃኑ በላይነህ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የፌዴሬሽኑ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና የድሬድዋ ከተ/አስ/አት/ፌዴሬሽን አመራሮች ተገኝተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫውን ሰጥተዋል።
ኮ/ር ማርቆስ የዘንድሮው ውድድር የሚደረግበት ወር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት ከሚከበርበት ወር ጋር በመገጣጠሙ ልዩ መሆኑና ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችን አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀው ስፖርት ከዘር፣ ከሀይማኖት ከሌሎች ተፅእኖዎች ነፃ መሆኑን ገልፀው ለሃገራዊ አንድነት ሚናው የጎላ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አቶ አስፋው ዳኜ በበኩላቸው ውድድሩ አስመልክቶ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን አንስተዋል፣ ኮ/ር ብርሃኑ በላይነህ ድሬዳዋ ላይ ይሄ ውድድሩ መካሄዱ ለከተማው አትሌቲክስ መነቃቃት የሚፈጥር ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ውድድሩን ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልፀዋል።
ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ በነበረ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ እና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልማትና እድገት ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ክቡር አቶ አበዱሰላም መሃመድ፣ ከኮማንደር ብርሃኑ በላይነህ የድሬዳዋ ከ/አስ/አት/ፌ/ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የኢአፌ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በተካሄደ ውይይት በአጫጭር ርቀቶችና በሜዳ ተግባራት ላይ ከተማ አስተዳደሩ አደረጃጀቱን ከማጠናከር ጎን ለጎን በትኩረት በመስራት ለለውጥና ለውጤት መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ በውይይቱ ወቅት በሰጡት አስተያየትም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 5 እና ከ5 በላይ ክለቦችን በማደራጀት ህልውናቸውን ማስጠበቅ፣ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ውጤታማ በመሆን የአትሌቲክሱ ሪፎርም አካል መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል። አያይዘውም የኢአፌ አቅሙ በፈቀደ መጠን በማንኛውም መልክ የከተማሪዎች አአስተዳደር አተሌቲክስ ፌዴሬሽንን እንደሚደግፍ አስታውቀዋል። አክለውም በሶማሌና በሐርሪ ክልሎችም በመገኘት ተመሳሳይ ውይይቶች መደረጋቸውንና የአትሌቲክሱ አመራሮች ቁርጠኝነት ማሳየታቸውን ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ ማለዳ ላይ በድሬዳዋ ስቴድዮም በመገኘት የታዳጊ አትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞችን አነጋግረዋል።
ሰልጣኞቹ አለብን ያሏቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን የኢአፌ የሥራ አስ/ኮ/አባላት ወ/ሮ ሳራ ሃሰን፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስና አቶ ቢልልኝ መቆያ ለተነሱት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች በየተራ ምላሽ ሰጥተዋል።
በሌላ ዜና 14ኛውን የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድርና ለ125ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል በማስመልት በድሬዳዋ ከተማ በልዩ ልዩ ጣእመ ዜማና በማርሽ ባንድ የታጀበ የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ ይገኛል። አትሌቲክሱ እንደ አድዋ ድል ሁሉ የህብረ ብሄራዊነት መገለጫ መሆኑ የሚያመሳስላቸው ጉዳይ ነው።
Similar Posts
Latest Posts from