በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ የኢአፌ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ፣ ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ ኮ/ር ማርቆስ ገነቲ፣ አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢአፌ የጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ አስፋው ዳኜ የተሳትፎና ውድድር ንኡስ የስራ ሂደት መሪ፣ የፌዴሬሽኑ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን።
በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳድሮች፣ ክለቦች እና ውድድሩን ለመምራት ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተመረጡ ዳኞች ተገኝተዋል።
በቴክኒካዊ ስብሰባው ላይ ውድድሩን የተመለከቱ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ማለትም የሽልማት አሰጣጥ ሰነስርዓትና አለባበስ፣ በውድድር ወቅት ስለሚኖር ሪፍሬሽመንት፣ የፀጥታ ሁኔታና፣ አጠቃላይ ከኮቪድ-19 መከላከል አንፃር ስለሚኖር የጥንቃቄ ፕሮቶኮል በዋናነት ተነስቶ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በተለይም የውድድር የዳኝነት ሂደቱን አስመልክቶ አቶ ቢልልኝ መቆያ ከዚህ በኋላ በሚደረጉ ውድድሮች ጥራታቸውን ለማስጠበቅ ብቃት ያላቸውንና ዓለም አቀፍ ስልጠና የወሰዱ ዳኞችን እንደሚመደቡ የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ይሄንን ውድድር ለየት የሚያደርገው ከአድዋ ድል 125ኛ ዓመት በሚከበርበት ወቅት በበረሃዋ ገነት ድሬደዋ ከተማ መከበሩ መሆኑን አስታውቀው ውድድሩ ከጠዋት 12:30 ጀምሮ ለተመልካች ክፍት ይሆናል ብለዋል፤ እንዲሁም ዘንድሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮን 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ ክብረ በዓል በልዩ ሁኔታ ለማክበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

 

Similar Posts
Latest Posts from