ውድድሩ ከተጀመረ ስድስተኛ ቀኑንና የመጨረሻው የሆነውን የኢትዮጵያ የክለቦች አጭር፣ የመካከለኛ ፣የሜዳ ተግባራትና እርምጃ ሻምፒዮና በዛሬው እለት ተፈፅሟል፡፡
በእለቱ ለአሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማት ከመሰጠቱ በፊት የውድድሩ ድምቀት ከነበሩት ውስጥ አንደኛው የመከላከያ ክለብ አባላት በሁለቱም ፆታዎች ያሸነፉበትን ሽልማት መታሰቢያነቱን በቅርቡ ሀገር ሲጠብቁ ለተሰዉ የመከላከያ ሃይል አባላት እንዲሆን በማድረግና ተመልካቹ ከመቀመጫው ተነስቶ የሻማ ማብራትና የህሊና ፀሎት የማድረስ ስነ-ስርዓት በማካሄድ ነበር፡፡
የሜዳሊያ ሽልማቶቹን በእለቱ የክብር እንግዳ የነበሩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንትና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ ናቸው፡፡
የኢ.አ.ፌ ፕሬዝደንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና የሀገር መከላከያ ሚ/ር የኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ ዋና ዳይሬክትር የሆኑት ሜ/ጀነራል መሃመድ ተሰማ በዕለቱም ለአሸናፊዎች ዋንጫዎችን የሸለሙ ሲሆን በአጠቃላይ ውጤትም መከላከያ በወንድም በሴትም አንደኛ፣ የኢት/ንግድ ባንክ በወንድም በሴትም ሁለተኛ እና ሲዳማ ቡና ክለብ እንዲሁ በወንድም በሴትም የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ነው፡፡
 
አጠቃላይ ነጥባቸው በዝርዝር ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
 
Similar Posts
Latest Posts from