በወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ባለውና ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ የክለቦች አጭር ፣ መካከለኛ፣ የሜዳ ተግባራትና የእርምጃ ውድድር ሻምፒዮና ዛሬም የተለያዩ የአትሌቲክስ ስፖርት የፍፃሜ ውድድሮችን አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
በሴቶች ምድብ በተደረገው የስሉስ ዝላይ ውድድር
ነፃነት ኦቦሌ ከመከላከያ ክለብ 12.56 በመዝለል 1ኛ
አርያት ዲቦ ከሃዋሳ ከተማ ክለብ 12.46 በመዝለል 2ኛ እንዲሁም
አጁዳ ኡመድ ከመከላከያ ክለብ 12.41 በመዝለል 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ ቀጣዩ መርሃ- ግብር የነበረው በወንዶች መካከል የተደረገው የአሎሎ ውርወራ ሲሆን በውጤቱም፡-
ዘገዬ ሞጋ ከኢት/ንግድ ባንክ 14.91 በመወርወር 1ኛ
መኩሪያ ኃይሌ ከቡራዮ ከተማ ክለብ 13.51 በመወርወር 2ኛ
ጆን ኡባንግ ከመከላከያ ክለብ 12.84 በመወርወር 3ኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ ቀጣዩ መርሃ-ግብር የ800ሜ የሴቶች ምድብ የሚከተሉት ውጤቶች ሲመዘገቡ
ወርቅውሃ ጌታቸው ከመከላከያ ክለብ 2፡02.40 በመግባት 1ኛ
ቅሳነት አሶም ከኢት/ንግድ ባንክ 2፡04.10 በመግባት 2ኛ
ወዛም አረፈአይኔ ከኢት/ንግድ ባንክ 2፡04.55 በመግባት የ3ኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ
በወንዶች የ800ሜ ምድብ ደግሞ ውጤቶቹን ስናይ
ዳንኤል ወልዴ ከዘቢደር ክለብ 1፡48.34 በመግባት 1ኛ
ጫላ ደፋሌ ከኦሮ/ውሃ ስራዎች 1፡48.96 በመግባት 2ኛ
ጡሪ ሞርከና ከኦሮ/ደንና ዱር ክለብ 1፡49.48 በመግባት 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ መጠናቀቂያ መርሃ-ግብር መሰረት መጨረሻ ላይ የተካሄደው ውድድር የ4×400 ሜ የድብልቅ ሪሌ ሲሆን በውጤቱም
ኢት/ኤሌክትሪክ ክለብ በቡድን ውጤት 3፡28.23 በመግባት 1ኛ
መከላከያ ክለብ በቡድን ውጤት 3፡33.39 በመግባት 2ኛ እንዲሁም
ኦሮሚያ ፖሊስ ክለብ በቡድን ውጤት 3፡40.40 በመግባት የ3ኛ ደረጃን በመያዝ የዛሬው
የውድድር መርሃ-ግብር ለሁሉም አሸናፊ ክለቦች የሽልማት ስነ-ስርዓትን በማድረግ ተጠናቋል፡፡
Similar Posts
Latest Posts from