ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ሲካሄድ ቆይቶ የዛሬው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሰረት በሴቶች 400ሜ መሰናክል :-
• መስከረም ግዛው ከቡራዮ ከተማ 1፡01.70 በመግባት 1ኛ
• ገበያነሽ ገዴቻ ከመከላከያ ክለብ 1፡02.77 2ኛ
• ምህረት አሻሞ ከመከላከያ 1፡03.24 በመግባት 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ በወንዶች 400ሜ. መሰናክል ምድብ ደግሞ
• ደረሰ ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 51.58 በመግባት 1ኛ
• ጋዲሳ ባዮ ከቡራዮ ከተማ 52.37 በመግባት 2ኛ
• ሀባታሙ ሀጎስ ከሲዳማ ቡና 53.09 በመግባት 3ኛ በመውጣት ሲጠናቀቅ ውድድሩበወንዶች ምድብ ቀጥሎ በዲስከስ ውርወራ ፡-
• ምትኩ ጥላሁን ከመከላከያ 44.47 በመወርወር 1ኛ
• ገበየሁ ገ/የሱስ ከኢት/ንግድ ባንክ 44.19 በመወርወር 2ኛ
• ጌታቸው ተመስገን ከመከላከያ ክለብ 43.52 በመወርወር የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡7
ከፍተኛ ፉክክር ከታየበት የወንዶችና የሴቶች የ100 ሜ. ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ
• ጀንካ ለቢሶ ከመከላከያ 10.59 በመግባት 1ኛ
• ሎጀ ኪደንግ ከሲዳማ ቡና 10.68 በመግባት 2ኛ
• አብዶ ዋሲሁን ከአማራ ማረሚያ 10.72 በመግባት 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቅ
በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር ደግሞ፡-
• የአብስራ ጃርሶ ከኢት/ንግድ ባንክ 11.91 በመግባት 1ኛ
• ራሄል ጌታቸው ከኢት/ንግድ ባንክ 1198 በመግባት 2ኛ እንዲሁም
• ፋዬ ፍሬይሁን ከመከላከያ 12.09 በመግባት የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ የውድድሩ የመጨረሻ ዝግጅት የነበረው በሴቶች ምድብ የተካሄደው የከፍታ ዝላይ ሲሆን በውጤቱም፡-
• አርአያት ዲቦ ከሃዋሳ ከተማ 1.75 በመዝለል 1ኛ በመሆን ስታጠናቅቅ
• ኛጃክ ማች ከኢት/ኤሌትሪክ 1.65 በመግባት ሁለተኛ
• ኝሪያክ ኙት ከሲዳማ ቡና 1.60 እንዲሁም
• አጁዳ ኡመድ ከመከላከያ 1.60 ሁለቱም በተመሳሳይ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡
በመጨረሻም ትናንት የተካሄደውንና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኙት ውድድሮች በሙሉ የሽልማት ስነ-ስርዓት በማድረግ የዛሬው መርሃ-ግብር በወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ተጠናቋል፡፡
 
 
Similar Posts
Latest Posts from