በኮሮና ውስጥ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የሀገር ውስጥ የትራክ ውድድር ከታህሳስ 13-18 የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር ፣መካከለኛ፣እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስቴድየም ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በእለቱም ከተካሄዱት ውድድሮች መካከል የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን ከነዚህ መካከልም የአሎሎ ውርወራ በሴቶች እንዲሁም በወንዶች የስሉስ ዝላይ ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል፡፡
በሴቶች ምድብ በተደረገው የአሎሎ ውርወራ አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀችው የመከላከያ ክለቧ ዙርጋ ኡስማን 12.30 የወረወረች ሲሆን ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀችው አይናለም ነጋሽ በድጋሚ ከመከላከያ 11.84 በመወርወር ሲሆን የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችው የደቡብ ፖሊስ ክለብ ተወዳዳሪ የሆነችው ሰላማዊት ማሬ 11.48 በመወርወር ነው፡፡
በወንዶች ምድብ በተካሄደው የስሉስ ዝላይ ውድድር አዲር ጉር ከመከላከያ ክለብ 15.42 በመዝለል አንደኛ በቀለ ጂሎ ከአዳማ ከተማ 15.31 የዘለለ ሲሆን ብርሃኑ ሞሲሳ ከፌደራል ማረሚያ 14.99 በመዝለል የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡
ያለ ውድድር ረጅም ጊዜያትን ያሳለፉት አትሌቶችና አሰልጣኞ ይህ ውድደር በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ውድድሩ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ፡፡
Similar Posts
Latest Posts from