የምርጫ ውጤት ማስተካከያ፣
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትላንትናው እለት ባካሄደው 24ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ ማድረጉ ይታወቃል።
ነገር ግን በአንዳንድ ብዙሃን መገናኛ በብቸኝነት ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በተሰጠው ድምፅ በአንድ ተቃውሞ ተመርጠዋል ብለው እየዘገቡ ሲሆን ይህ ፈፅሞ ስህተት እና በድምፅ አሰጣጥ ወቅት በምርጫ ወረቀት ላይ ድምፅ ሰጪው የራይት ምልክት ማድረግ ሲገባቸው የኤክስ ምልክት በማድረጋቸው መሆኑ ታውቆ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ድምፅ ባላቸው የጉባኤ አባላት በሙሉ ድምፅ ያለምንም ተቃውሞ ለፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ያሸነፋ መሆኑን ታውቆ አየተዘገቡ ያሉ የስህተት ዜናዎች እንዲታረሙ እናሳስባለን። የስፖርት ቤተሰቡም ይህንን እንዲረዳ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
  
 

 

Similar Posts
Latest Posts from