ድንቅ ዝክረ መርኃ ግብር በሸራተን አዲስ፣
የሻምበል አበበ ቢቂላ 60ኛ አመት የሮም ኦሊምፒክ የማራቶን ድልና ከሜልበርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ የተሳተፉ የአትሌቲክስ ጀግኖች ዛሬ ታሀህሳስ 4/2013 ዓም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ክብርት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት፣ ክቡር አቶሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ብሄ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት፣ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሣው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ምገስ የትራንስፖርት ሚ/ር ሚኒስትር፣ ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት፣ ክብርት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንትና የስራ አሰ/ኮ/ አባላት፣ ክቡር አቶ አብነት ገ/መስቀልና በርካታ ስመጥር የክብር እንግዶች፣ በኦሊምፒክ የአትሌቲክስ ስመጥር ጀግኖችና ቤተሰቦች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተዘክረዋል።
ከሜልበርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ፣ ከተሳታፊ እስከ ወርቅ ባለድል አትሌቶች፣ በህይወት ያሉ በአካል፣ የሌሉ በቤተሰቦቻቸው አማካይነት ሁሉም የተዘጋጀላቸውን የምስጋና ዋንጫ፣ እንዲሁም ፌዴሬሽኑ ያዘጋጀውን ከሜልበርን እስከ ሞስኮ ኦሊምፒክ ለተሳተፋ አትሌቶች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ተረክበዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሣህለወርቅ፣ ክብርት ዶ/ር ሂሩት፣ እና ክብርት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ በየተራ ዝግጅቱን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ስፖርት በተለይም አትሌቲክስ የሰላምና የአንድነት መሠረት መሆኑን አስምረውበታል።
መርኃ ግብሩ በኢቢሲና በኦቢኤን በቀጥታ ለ2 ሰዓታት ተላልፏል።
 
 
Similar Posts
Latest Posts from