የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ታህሳስ 3/2013 ዓ.ም ከማለዳው 2:30 ላይ ጉርድሾላ ዋናው ቢሮ ጎን ለሚያስገነባው ባለ 12 ወለል ሁለገብ ዘመናዊ ህንፃ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።
የመሠረት ድንጋዩን ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ም/ፕሬዝዳንትና ክቡር አቶ ኤልያስ ሽኩር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በጋራ አስቀምጠዋል።

በመቀጠልየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያሰራው 1.6 ኪሎ ሜትር የአትሌቲክስ አሸዋ ትራክ ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት፣ ክቡር አቶ ሐብታሙ ሲሳይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ክቡር አቶ ኤልያስ ሽኩር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት፣ ክብርት ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የለጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስ/ከንቲባ፣ የክልልና ከተማ አስ/አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ ስመጥርና ጀግኖች አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የአትሌቶች ቤተሰቦችና ጥሪ የተደገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመልዕክታቸው የአገራችን መገለጫ የሆነውን አትሌቲክሳችንን ለማልማት የማዘውተሪያ ስፍራዎች በየቦታው ደረጃውን ጠብቆ መገንባት መሰረታዊ በመሆኑ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በተመሳሳይ በቀሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ መውጫ ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች ቦታዎችን በማዘጋጀት ከፌዴሬሽኑ ጋር ማዘውተሪያዎችን ለመስራት ቃል ገብተዋል።
 
Similar Posts
Latest Posts from