ይህ እለት ቅዳሜ ህዳር 05/2013 ዓ.ም. በሙኒክ ኦሊምፒክ እ.ኤ.አ በ1972 በአትሌቲክስ ተሳትፎና ድል ኢትዮጵያን ከአለም ጋር ያስተዋወቁ የአትሌቲክስ ጀግኖች ቀን ነው፡፡
በኢትዮጵያ አቆጣጥር ከነሃሴ 20/1964 እስከ መስከረም 01/1965ዓ.ም. በጀርመን ሙኒክ ከተማ ለ20ኛ ጊዜ በተካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሃገራችን ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ሃያ ወንድ አትሌቶች በአጭር፣ በመካከለኛ፣ በረጅም ርቀቶች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በሪሌ እና በ3ሺ ሜ.መሰ. እንዲሁም በማራቶን የውድድር ተግባራት ለመሳተፍ ተመርጠው በወቅቱ አሰልጣኝ በነበሩት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬና በአሰልጣኝ ንጉሴ ሮባ አማካይነት ዝግጅታቸውን አከናውነው ወደ ውድድሩ ስፍራ ተጉዘዋል፡፡
በሙኒክ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በማራቶን በሻምበል ማሞ ወልዴ እና በ10000 ሜትር በሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በተገኙ ሁለት የነሃስ ሜዳልያዎች በኦሎምፒኩ ላይ ከተሳተፉ የዓለም ሃገራት በአትሌቲክስ 17ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ በዚህ ኦሎምፒክ ላይ የሮምና የቶኪዮ ባለድል ሻምበል አበበ ቢቂላ በውድድር ስፍራ ላይ በክብር እግድነት ተጋብዞ ውድድሩን ተከታትሏል፡፡
የማሞና ምሩፅ ነሃሶች፣
በፌደራል ሪፐብሊክ ጀርመን – ሙኒክ ከተማ በተካሄደው የ1972 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ሻምበል ማሞ ወልዴ በኦሎምፒከ ጨዋታ በማራቶን ለተከታታይ ሶስት ጊዜያት በተካሄዱ ኦሎምፒኮች ተሳትፎ በሜክሲኮ ካስመዘገበው ድል በኋላ 2፡15፡08 በሆነ ሰዓት የነሃስ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡ በተመሳሳይም ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ለመጀመሪያ ጊዜ በነበረው የኦሎምፒክ ተሳትፎ በ10ሺ ሜትር 27፡40.96 በሆነ ሰዓት የነሃስ ሜዳልያ አግኝቷል፡፡
እለቱን በጋራ እንዘክረው፤
Similar Posts
Latest Posts from