ይህ እለት ማክሰኞ ህዳር 1/2013 ዓ. ም. በሜልበርን ኦሊምፒክ እ.ኤ.አ በ1956 በአትሌቲክስ ተሳተፎ ኢትዮጵያን ከአለም ጋር ያስተዋወቁ የአትሌቲክስ ጀግኖች ቀን ነው፡፡
በኢትዮጵያ አቆጣጥር ከህዳር 14-22/1949 ዓ.ም. በአውስትራሊያዋ ሜልበርን ከተማ ለ16ኛ ጊዜ በተካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአትሌቲክስ በስምንት ወንድ አትሌቶች በአጭር፡ በመካከለኛ ርቀቶችና በማራቶን የውድድር ተግባራት ለመሳተፍ የተመረጡት አትሌቶች በደብረዘይት አየር ኃይል ካምፕ ውስጥ ለ2 ወራቶች በወቅቱ አሰልጣኝ በነበሩት በስውዲናዊው ካፕቴን ላርሰን ዝግጅታቸውን አድርገው ወደ ውድድር ስፍራዉ ተጉዘዋል፡፡
በዚህ ኦሎምፒክ በማራቶን የተካፈሉትና ውድድራቸውን 29ኛ እና 32ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ባሻዬ ፈለቀ እና ገብሬ ብርቄ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች እንደ ሃገር ተካፍላ በፍፃሜ ውድድር ላይ የተሳተፉና ያጠናቀቁ በመሆን ስማቸውን በደማቁ ማፃፍ የቻሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ስድስት ተወዳዳሪዎች በአጭር፣ በመካከለኛና በሪሌ የውድድር ተግባራት ላይ በማጣሪያ ውድድሮች የተሳተፉ የመጀመሪያዎቹ አትሌቶች ናቸው፡፡
በወቅቱ ቡድኑን ይዘው የተጓዙ ልዑካን ቡድን አባላት፡-
1. የቡድን መሪ ፡- አቶ ይድነቃቸው ተሰማ
2. ም/ ቡድን መሪ ፡- አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ
3. አሰልጣኝ፤- ስዊድናዊ ካፕቴን ላርሰን
በጋራ እንዘክረው፤

 

 

&

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Similar Posts
Latest Posts from