የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ያስገነባው የማዘውተሪያ ስፍራ ተጎበኘጥቅምት 14/2013 ዓ.ም.
የኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የለገጣፍ ለገዳዲ ከተማ ከንቲባ፣ ዶ/ር መስፍን አሰፋ የቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዴኤታና የቀድሞ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጎበኘ።
በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ/ም/ፕሬዝዳንት ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ስለ ማዘውተሪያ ስፍራው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተገነባውን የአሸዋ ጥርጊያ ሜዳ ከ1.6 ኪሜ ወደ 2 ኪሜ ለማሳደግ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ለከተማዋ ከንቲባ አቅጣጫ ሰጥተዋል ግንባታው እያከናወነ የሚገኘው የካንትሪ ክለብ ፕሬዝዳት ዶ/ር ኢንጂነር መሰለ ኃይሌ ግንባታውን ለማከናወን ፈቃደኝነታቸው ገልፀዋል። እንዲሁም ክቡር ፕሬዝዳንቱ በሌሎች ስፍራዎች ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎችን ለመገንባት ፌዴሬሽኑ አቅም ካለው የክልሉ መንግስት ቦታዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ለአትሌቲክሱ ልማት ሁሌም ከፌዴሬሽኑ ጎን እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።
በዚህ ጉብኝት መርሀ ግብር ላይ አቶ አድማሱ ሳጂ፣ አቶ ፈሪድ መሀመድ ፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የሲድኒው ጀግና አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና አቶ አስፋው ዳኜ የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተር ተገኝተዋል።
Similar Posts
Latest Posts from