ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም. በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልኡካን ቡድን ለገጣፎ በሚገኘው ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል የፌዴሬሽናችን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ በተገኙበት አሸኛኘት ተደርጎለታል።
ፕሬዝዳንቷ በመልካም ምኞታቸውም በሰልጠና ያገኙትን ልምድ በቡድን ስራ እንዲያሳዩ አደራ ካሉ በኋላ በድል እንዲመለሱ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በሽኝቱ ላይ የአትሌቶች፣ የአሰልጣኞች፣ የዳኞች ማህበራት አመራሮች፣ ታዋቂ አሰልጣኞችና ማናጀሮች ተገኝተዋል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችና አሰልጣኞች ጥሩ ልምምድ አድርገው ለውድድር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅዳሜ ጥቅምት 07/2013 ዓ.ም. በፖላንድ ጊዲኒያ ለ24ኛ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ሃገራችንን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ የማጣሪያ ውድድር በማካሄድ ለአንድ ወር የሚሆን ጊዜ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶል እንሆ ዛሬ ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም. በድል ተመለሱ የሽኝት መርሃ ግብር ተከናውኗል ፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ላይ በሁለቱም ፆታ የምንሳተፍ ሲሆን ሃገራችንን የሚወክሉ አትሌቶች፡-
በወንዶች
1ኛ ሀይለማርያም ኪሮስ ከበደው
2ኛ አንዱዓምላክ በልሁ በርታ
3ኛ አምደወርቅ ዋለልኝ ታደሰ
4ኛ ጉዬ አዶላ ኢዳሞ
5ኛ ልኡል ገ/ስላሴ አለሜ
በሴቶች
1ኛ ያለምዘርፍ የኋላው ደንሳ
2ኛ ነፃነት ጉደታ ከበደ
3ኛ ዘይነባ ይመር ወርቁ
4ኛ አባበል የሻነህ ብርሃኔ
5ኛ መሰረት ጎላ ሲሳይ
ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 07/2013 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ሰዓት አቆጣጠር ከዚህ በታች ባለው መርሃ ግብር መሰረት ይከናወናል፡
11፡00 የሴቶች ግማሽ ማራቶን
12፡30 የወንዶች ግማሽ ማራቶን
መልካም እድል ለውድ አትሌቶታችን!!!
Similar Posts
Latest Posts from