ከኛ ወደ እኛ!
የአለም አትሌቲክስ የማይታመን ብሏል ተደንቆ፣
በስፔን ቫሌንሽያ ከተማ ትላንት መስከረም 27/2013 ምሽት ላይ በተደረገ የሩጫ ውድድር ሁለት የአለም ክብረወሰኖች ተሻሻሉ….
በሴቶች መካከል በተደረገ የ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 14:06:65 በሆነ ሰዓት በመግባት በርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት መሆን ችላለች።
በ5,000 ሜትር ሴቶች ሪከርዱ ለ12 አመታት በጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የቆ ቢሆንም የእኛዋ ሌላኛዋ ጀግናችን አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሪከርዱ ከሃገራችን እንዳይወጣ ማድረግ ችላለች፡፡
ይህ የለተሰንበት አኩሪ ድል ለበርካታ ኢትዮጵያውን አትሌቶች የይቻላል ምሳሌ የሚሆንና የሚያኮራ በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ለተሰንበት ግደይ አሁን በድጋሜ እንኳን ደስ አለሽ፤ እንኳን ደስ አለን! በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
በ10000 ሜትር ክብረወሰን ለ15 ዓመታት ያህል ተይዞ የቆየው በምርጡ አትሌታችን ቀነኒሳ በቀለ ነበር።
በትላንትናው እለት በቫሌንሽያ በተደረገ የ10,000 ሜትር ውድድር ኡጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴንጊ 26:11:00 በሆነ ግዜ በመግባት ክብረወሰኑን አሻሽሏል።
አትሌቱ ነሃሴ ወር ሞናኮ ላይ የ5000 ሜትር የዓለም ክብረወሰንን ማሻሻሉ ይታወሳል።
ለመላው የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አለን!!
Similar Posts
Latest Posts from