አስቸኳይ ማስታወቂያ!
በመላው አለም እና በእኛም ሃገር የዜጎች ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሃገራት ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን እያስተላለፉ ይገኛል፡፡
በእኛም ሃገር የኢፌዲሪ መንግስት ዛሬ መጋቢት 7/2012 ዓ. ም ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ሌሎች ጉዳዮች ጋር አያይዞ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርት ስልጠናዎችና ውድድሮችን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ያስታውቃል፡፡
ይህ ውሳኔ በሁሉም የፌዴሬሽኑ ባለድርሻዎች ዘንድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባዋል፡፡